በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሥልጣናቸውና ከፓርቲ መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ


Prime Minister of Ethiopia Hailemariam Desalegn
Prime Minister of Ethiopia Hailemariam Desalegn

ጠቅላይ ኢኒስትሩ በዛሬው ዕለት ለመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መገልጫ ያቀረቡት መልቀቂያ በፓርቲያቸው ደህዲንና በኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታውቀዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚጠብቁም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክኒያታቸውን ሲያስረዱ፤ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የተከሰተውን አለመረጋጋት ለመመቅረፍ የተለያዩ ለውጦችን ለማድረግ መጀመራቸውን ገልፀው፤ “ኢሕአዴግና መንግሥት እነዚህ ሪፎርሞች ለማሳካት ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ላይ እንገኛለን ለእነዚህ ሪፎርሞች መሳካትም ሆነ ላስቀመጥናቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች የመፍትሔው አካል ለመሆን በማሰብ በገዛ ፍላጎቴና ፈቃዴ የኢሕአዴግ ኃላፊነቴም ሆነ የመንግሥት ኃላፊነቴን ለመልቀቅ ትያቄ አቅርቤያለሁ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘው ፓርቲያቸው ደህዲንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያቀረቡት ጥያቄ እንደተቀበሏቸው ገልፀው ውሳኔ የሚያገኘው በቅርቡ በሚሰበሰበው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ይሆናል ብለዋል።

በመንግሥት በኩል ያለውን ሥልጣናቸውን በተመለከተ፤ “ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነቴን ለመልቀቅ የጠየኩትን ጥያቄ ይቀበለዋል የሚል እምነት አለኝ እነዚህን ጥያቄዎች ያቀረብኩበት ዋናው ምክኒያት በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለማድረግ የመፍትሔው አካል መሆን አስፈላጊ ነው ብዬ ስላመንኩ ነው። ሕዝቡ ለሚያነሳቸው በርካታ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ተገቢና አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ።” ብለዋል።

ውሳኔው እስኪፀድምቅ በኃላፊነታቸው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትርም ፍፁም ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የሚተካቸውን ይመረጣል ብልው እንደሚያልሙ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG