No media source currently available
የአለም አቀፉ የፍልሰት ቀን ትላንት ተከብሮ ውሏል። በኢትዮጵያም በአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት IOM አማካኝነት ለአንድ ሳምንት ስደተኞችን በሚመለከቱ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ነበር ። በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የስደት ድርጅት IOM የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ሰይፈስላሴ ‘በፍልሰት የተሰራች አለም በሚል መሪ ቃል’ ቀኑ ተከብሮ እንደዋለ ገልፀውልናል።