ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚከሰቱ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ወይም ጥቃቶች በቀጥታ በብሔር ላይ የተነጣጠሩ ናቸው የሚሉ አስተያየቶች በፍጥነት ሲሰራጩ ይሰማል።
ከጥቃቱ በኋላ መረጃዎች ሲጣሩ ደግሞ የጠፋው የሰው ሕይወት፣ የተጎዳውና የወደመው ንብረት በአካባቢዎቹ ላይ የሚኖሩ የተለያዩ የጎሳ ምንጭ ያላቸው ማኅበረሰቦችን ያጠቃ ሆነው መገኘታቸው ያመዝናል።
ባሳለፍነው እሁድ በወልዲያ ከተማ በመቀሌ ከነማና ወልዲያ ከነማ ተጫዋቾች ቡድን ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረውን መነሻ በማድረግ ጽዮን ግርማ ሁለት እንግዶችን አወያይታለች።
እንግዶቹ በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በተደጋጋሚ በመጻፍ የሚታወቀው የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምሕሩ ስዩም ተሾመና የአረና ትግራይ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አምዶም ገ/ሥላሴ ናቸው።
የውይይቱን ሙሉ ክፍል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ