በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ቃለ መሃላ ፈጽመው በትረ ሥልጣኑን ተረክበዋል


“ፈርማጆ” በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት አዲሱ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ቃለ መሃላ ፈጽመው በትረ ስልጣኑን ተረክበዋል። በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ሀገሪቱን ለማረጋጋት፣ ሰላም ለማስፈንና በአሁኑ ወቅት በርካታ ዜጎችን ለተረጂነት ያጋለጠው ድርቅ ያስከተለውን ረሃብ ለመቋቋም ሕዝቡ፣ መንግስቱና አጋሮቻቸው አብረው እንዲሠሩ ጠይቀዋል

በዚህ ዓመት በከፍተኛ ድርቅ የተጠቃችውና ለሁለት ዐስርት ዓመታት የዘለቀ ጦርነት ላይ የቆየችው ሶማሊያ አዲስ የፖለቲካ ምእራፍ ገጽ ገልጣለች።

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ቃለ መሃላ ፈጽመው በትረ ሥልጣኑን ተረክበዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:36 0:00

ፕሬዝደንት አብዱላሂ ፈርማጆ
ፕሬዝደንት አብዱላሂ ፈርማጆ

ፕሬዝደንት አብዱላሂ ፈርማጆ በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን የተያዙ ጥረቶችን ለማሳካት ዜጎቻቸው እንዲያግዟቸው በመጠየቅ ነው ሀገሪቱን መምራት የጀመሩት።

በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ሀገሪቱን ለማረጋጋት፣ ሰላም ለማስፈንና በአሁኑ ወቅት በርካታ ዜጎችን ለተረጂነት ያጋለጠው ድርቅ ያስከተለውን ረሃብ ለመቋቋም ሕዝቡ፣ መንግሥቱና አጋሮቻቸው አብረው እንዲሠሩ ጠይቀዋል።

የሶማሊያን አቢይ ፈተናዎች አብረን እንድንወጣ እባካችሁ እርዱኝ። ደህንነታችንን ማስጠበቅ፣ ድርቅን መዋጋትና የህግ የበላይነትን ማስከበር አለብን። የፍትህ ስርዓቱን በማሻሻል በስራ ላይ ማዋልና እርስ በርስ ይቅር የምንባባልበትና የጋራ መግባባትን ያሰፈኑ አራት የስልጣን ዘመናት ከእናንተ ጋር በመተባበር ለማሳካት እንሠራለን።

በዛሬው ዕለት በሞቃዲሹ አየር ማረፊያ የተካሄደው የቃለ መሀላ ስነስርዓት ላይ ሶስት የአካባቢው ሀገሮች መሪዎችና የ120 ሀገሮች ወኪሎች ተገኝተዋል።

የቪኦኤ ሶማሊኛ ዝግጅት ክፍል ያጠናቀረውን ዘገባ ሔኖክ ሰማእግዜር ያቀርበዋል።

XS
SM
MD
LG