በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሶማሊያዊ ወጣት ጉዳት አደረሰ


ፖሊስ-በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሶማሊያዊ ወጣት ጉዳት ባደረሰ ወቅት
ፖሊስ-በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሶማሊያዊ ወጣት ጉዳት ባደረሰ ወቅት

በዩናይትድ ስቴትስ ኦሃዮ ግዛት ዋና ከተማ ኮሎምበስ በሚገኝው የኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሶማሊያዊ ወጣት ጉዳት አደረሰ፡፡

ስሙ አብዱልራዛቅ መሆኑ የተነገረው የ18 ዓመት ወጣት ያሽከረክር የነበረውን መኪና ቆመው በነበሩ ሰዎች ላይ እየነዳ ከወጣ በኋላ፣ ከመኪና ውጥቶ በስለት መውጋት መጀመሩ ተዘግቧል፡፡

በጥቂቱ ዘጠኝ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን አጥቂው ግን መገደሉ ታውቋል፡፡

አድራጎቱ “የሽብር ጥቃት” ሊሆን እንደሚችል የኮሎምበስ ፖሊስ አዛዥ ኪም ጄከብስ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ነገ መደበኛ ትምህርት እንደሚቀጥል የኦሃዮ አገረ ገዥ ኛን ኬሲች ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG