በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒውዚላንድ ደቡባዊ ደሴት ዛሬ መሬት መንቀጥቀጥ ደረሰ


በኒውዚላንድ ደቡባዊ ደሴት በርዕደ መሬቱ የደረሠ ጉዳይ
በኒውዚላንድ ደቡባዊ ደሴት በርዕደ መሬቱ የደረሠ ጉዳይ

የኒውዚላንድ ደቡባዊ ደሴት ከሠዓታት በፊት በ7.8 በሚለካ ከባድ ርዕደ መሬት ተናግቶ ነበር።

የሀገሪቱ የሲቪል መከላከያ ሚኒስትር ገሪይ ብራውንሊ “ትልቁ ችግር መሠረት ልማቱ ይመስላል” ብለው ሲገለፁ ይህንንም የተናገሩትከጠቅላይ ሚኒስትር ጆን ኪ ጋር በመሆን ጉዳት የደረሰባቸውን ቦታዎች በአይሮፕላን ከተመለከቱ በኋላ ነው።

አንድ የውሀ ግድብ በርዕደ መሬቱ ምክንያት በደረሰበት ጉድት ምክንያት

“ክላርነስ” የተባለውን ወንዝ አግዶ ነበር፤ የወንዙ ውሀ ሞልቶ ቁልቁል በመፍሠሱ ሠዎች ወደ ከፍታማ ቦታዎች ለመሄድ ተገዱደዋል።

በኒውዚላንድ ደቡባዊ ደሴት በርዕደ መሬቱ የደረሠ ጉዳት
በኒውዚላንድ ደቡባዊ ደሴት በርዕደ መሬቱ የደረሠ ጉዳት

​በርዕደ መሬት ምክንያትመ የደረሰው ጉዳት ቢያንስ በሁለት ቢልዮን ዶላር የሚገመት እንደሚሆን ጆን ኪ ገልፀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የኒውዚላንድ ደቡባዊ ደሴት በደረሠው ርዕደ መሬት ጉዳትን በተመለከተ አስፈላጊ እርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን ቃል አቀባያቸው ጆን ከርቢ ጠቁመዋል።

XS
SM
MD
LG