No media source currently available
በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች የዉሃ አቅርቦቱ ከኤሌክትሪክ ሃይል ችግር እጥረት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ባለፈዉ ክረምት በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ግድቦች የሚጠበቀዉን ያህል ዉሃ እንዳልያዙና ያ ለእጥረቱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ባለስልጣናት ገልጸዋል። የዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የዉሃ ማደያ ጣቢያዎችን ከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። መለስካቸዉ አመሃ የአስኮ አካባቢ ነዋሪዎችና ዉሃ ማደያ ጣቢያ ሃላፊን አነጋግሮ ተከታዮን ዘግቧል።