በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


East Africa outline map
East Africa outline map

አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራምን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ብሪታንያ ተጨማሪ 30 ሚልዮን ፓውንድ ለኢትዮጵያ እንደምትሰጥ ታወቀ፣ በዎሎንኮሚ ኦሮሚያ የተፈጸመው ግድያ፣ ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር መተማመን የማዳበር ፍላጎት እንዳላት ገለጸች፣ ኬንያውያን ሙስሊሞች ክርስትያኖችን ከሞት አዳኑ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው ቅንብራችን የምንመለከተው።

ብሪታንያ በኢትዮጵያ ለተከሰተው ከባድ ድርቅ ተጨማሪ 30 ሚልዮን ፓውንድ እንደምትሰጥ ጋርዲያን ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ገልጿል። አለም አቀፍ የልማት ክፍል በገለጸው መሰረት የድርቁ ሁኔታ መራዘም በመጪው አመት አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ብዛት 18 ሚልዮን ሊደርስ ይችላል።

ብሪታንያ ከምትሰጠው ገንዘብ ግማሹ 1.9 ሚልዮን ለሚሆኑ ሰዎች የአስችኳይ ጊዜ ረድኤት ለማቅረብ እንዲችል ለአለም የምግብ ፕሮግራም ይሰጣል። 14 ሚልዮን ፓውንድ ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አገልግሎቶችና የአስቸኳይ ጊዜ ውሀና የጤና ጥበቃ አገልግሎት ለሚያቀርቡት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተደራሽ ይሆናል ሲል የጋርዲያን ድረ-ገጹ ጠቁሟል።

አሁንም ጋርዲያን በኦሮሚያ በሚካሄደው ተቃውሞ ስለተፈጸሙት ግድያዎች ዘግቧል። የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ሁለት አስከሬኖችን በብርድ ልብስና ብፕላስቲክ ጠቅልለው የሞቱት ስዎች ስሞች የተጻፉባቸው ወረቀቶች እላቸው ላይ አስቀምጠዋል። የገድልዋቸው ጥይቶች ቀለሆችም እዛው ይታያሉ። “ዲሞክራሲም ሆነ ፍትህ የለም” እያሉ የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ማስተጋብት ጀመሩ።

ይህ የሆነው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ወሎንኮሚ በተባለው ቦታ ላይ ነው የተፈጸመው።የጸጥታ ሃይሎች በአዲስ አበባ አከባቢ ያሉትን የእርሻ ቦታዎችን ለማልማት የታሰብውን እቅድ በመቃወም በተሰባሰቡት ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍቱ። ቢያንስ 4 ሰዎች ተገድለዋል ይላል ዘጋቢው።

ዐል-ሞኒተር የተባለው የግብጽ ጋዜጣ ጽረ-ገጽ ደግሞ ግብጽና ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በሚመለከት ልዩነት ቢኖራቸውም ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር የመተማመን መንፈስ የመገንባት ፍላጎት እንዳላት ጠቁሟል።

የግብጽ፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ የውሀ ሀብት ሚኒስትሮች ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሊያደርስ የሚችለው አደጋን በሚመለከት በቴትክኒካዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለመቻላቸው የድርድሩ ሂደት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ እንዲካሄድ መደረጉን የግንጽ የውሀ ሃብትና የመስኖ ጉዳይ ሚኒስትር ሐሳም ሞግሃዚ መናገራቸውን ዐል-ሞኒተር ጠቅሷል።

ሞግሃዚ አያይዘውም ግብጽ ከኢትዮጳያ ጋር በፖለቲካ ረገድ መተማመን ለመገንባት ቁርጠኛ ናት። ይሁንና የናየል ወይም የአባይ ወንዝ ውሀን በሚመለከት ያላትን ታሪካዊ መብት አትለቅም ማለታቸውን ድረ-ገጹ ጨምሮ ገልጿል።

ተጨማሪ ዘገባንም አካተናል። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:16 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG