በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና አፍሪቃን አስመልክቶ ያላቸው ትብብር


ሱዛን ቶርንተን በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ እስያና የፓሲፊክ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር
ሱዛን ቶርንተን በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ እስያና የፓሲፊክ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር

የዩናይትድስቴስ ባለስልጣኖች መንግስታቸውና ቻይና በአፍሪቃ ሰላማና ልማት እንዲኖር ስለሚፈልጉ በአህጉሪቱ አበረው እየሰሩ ነው ማለታቸውን የደቡብ አፍሪቃ ዘጋብያችን አኒታ ፓወል ከጆሀንስበርግ በላከችው ዘገባ ጠቅሳለች አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ዩናይትድስቴትስና ቻይና በአፍሪቃ ተደማጭነት ለማግኘት ሲፋጩ ቆይተዋል። ቻይና በመላ አፍሪቃ በምታደርገው ከፍተኛ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ምክንያት በአፍሪቃ ከሌሎች ሀገሮች ይልቅ የበላይነት ማግኘትዋ አልቀረም። ቻይና ከአፍሪቅ ጋር የምታደርገው የንግድ ልውውጥ ባላፈው አመት $220 ቢልዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ዩናይትድስቴትስ ከአፍሪቃ ጋር ከምታደርገው የንግድ ልውውጥ በሶስት እጥፍ ይልቃል።

ይሁንና ሁለቱ ሃገሮች በአፍሪቃ የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰትንና ዲፕሎማስያዊ ስራን ለማጠናከር በሚያደርጉት ጥረት ተቻችለው በመስራት ረገድ ደስተኞች መሆናቸውን በ ዩናይትድስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ እስያና የፓሲፊክ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሱዛን ቶርንተን ገልጸዋል።

የቻይናው ፕረዚዳንት ሺ ዢያንፒንግ በዩናይትድስቴት ስላካሄዱት ጉብኝት በያዝነው ሳምንት ለጋዜጠኖች ተናግረዋል።

“በመጀመርያ ደረጃ ዩናይትድስቴትስና ቻይና በአፍሪቅ ላይ ያላቸው ፍላጎት ተመሳሳይ ነው። ሁለታችንም አፍሪቃ ውስጥ ልማትና ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዲኖር እንሻለን። ስለሆነም ቻይና ለአፍሪቃ ሰላማና ጸጥታ የምታደርገውን አስተዋጽዕ በበጎ እንቀበለዋለን። ግጭት ባለብቸው የአፍሪቃ ሃገሮች ሰላም ጠባቂ ሃይሎችን ማስማራትዋንና በአፍሪቅ ቀንድ የባህር ላይ ውንብድናን በመከላከል ተግባር የቻይናን ተሳትፎ እንደግፋለን።”

ቻይና የኢቦላ በምዕራብ አፍሪቃ መስፋትን ለመገደብ ባደረገችው ጥረትና ጤናማ የሆነ የመዋዕለ-ነዋይ ህዋ እንዲኖር የሚረዳ የመሰረተ-ልማት ውጥን ማቅረባዋን ዩናይትድስቴትስ በበጎ ትመለከተዋለችም ብለዋል ባለስልጣንዋ።

የሳቸው አባባል ግን ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ሀምሌ ወር ላይ አፍሪቃን በጎበኙበት ወቅት ካሉት ጋር የሚቃረን ይመስላል። የኢኮኖሚ ግንኙነት ማለት የሀገሮችን መሰረተ ልማት በውጭ የሰው ሃይል መገንባታና የአፍሪቃን የተፈሮ ሃብት ማውጣት ማለት አይደለም ሲሉ ፕረዚዳንት ኦባማ ለአፍሪቃ መሪዎች ባደረጉት ንግግር ገልጸው ነበር።

ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

ዩናይትድ-ስቴትስ-ቻይናና-አፍሪቃ-11-6-15
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG