በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ገንዘቤ ዲባባ ቃሏን ጠበቀች


Genzebe Dibaba
Genzebe Dibaba

በቤይጂንጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 1,500m ድል ተቀዳጅታ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኘች።

ገንዘቤ በዚህ ርቀት ሞናኮ ላይ በቅርቡ አዲስ የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገቧ አይዘነጋም።

የገንዘቤ እህት ጥሩነሽ ዲባባ ከሰባት ዓመታት በፊት እ አ አ በ 2008 ዓም እዚሁ ቤይጂንግ Bird’s Nest ወይም የወፍ ጎጆ ስታዲየም በኦሊምፒክስ በ 5 እና በ 10 ሺህ ሩጫ ውድድሮች በሁለቱም የወርቅ ሜዳልያ በማግኘት ታሪክ ሠርታለች።

አሁንም ገንዘቤ እዚሁ ስታዲየም ውስጥ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 1, 500 እና በ 5,000 ሜትር ሩጫ ውድድሮች በሁለቱም ወርቅ ለማግኘት ዓልማለች።

የመጀመሪያውን ወርቅ ዛሬ ወስዳለች። ሁለተኛው የፊታችን ዕሁድ የሚታይ ይሆናል።

መልካም ዕድል እንመኛለን።

XS
SM
MD
LG