አዲስ አበባ —
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ከኣንድ ኣመት ተኩል በላይ የዘለቀውን የርስ በርስ ጦርነት ለማክተም የታለመውን የሰላም ውል ኣልፈርምም ማለታቸው ተዘገበ።
የፕሬዚደንቱ ውሳኔ የምስራቅ ኣፍሪካ ሃገሮች የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ በኣዲስ ኣበባ መንግስቱና ኣማጽያኑን በሚሸመግለው የሰላም ድርድር ላይ ሌላ እክል ደቅኗል።
የርስ በርስ ጦርነቱ ይቀጥላል ማለት ነው ወይ? ተብለው በቪኦኤ የተጠየቁት የኣማጺያኑ ቃል ኣቀባይ Stephen Par “ግልጽ ነው” ማለታቸው ተጠቅሷል።
ለሁለቱ ወገኖች የቀረበውን የሰላም ስምምነት የኣማጽያኑ መሪ ሪያክ ማሻር እና የገዢው ፓርቲ ሊቀመንበር ፓጋን ኣሙም ፈርመዋል። ሆኖም ፕሬዚደንቱ ውድቅ ያደረጉት ውል ትርጉም የሚኖረው እንደማይመስል ተመልክቱዋል። ፕሬዚደንት ኪር በመንግስታቸው የትዊተር መገናኛ ላይ ባወጡት መግለጫ “የማይዘልቅ ሰላም መፈረም ኣይቻልም። ዛሬ ፈርመን ነገ ውጊያ የምንገባ ከሆነ ምን ኣከናወንን ?” ማለታቸው ተገልጿል።
የአዲስ አበባው ዘጋብያችን እስክንድር ፍሬው ስለጉዳዩ ዋናውን አደራዳሪ አምባሳደር ስዩም መስፍንን አነጋግሯል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።