አዲስ አበባ —
ኢትዮጵያና አሜሪካ በፀጥታ ትብብር ጉዳይ ላይ ያላቸው ግንኙነት ልዩነት ባስነሱ ርዕሶች ላይ እንዲነጋገሩ እድል የሚፈጥር ነው ሲሉ አንድ የዘርፉ ተንታኝ አብራርተዋል።
የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ጉብኝትም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ልዩነት በሚፈጥሩት የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዲደረግ መንገድ የጠረገ እንደሆነ ተንታኙ ዶክተር መሃሪ ታደለ ማሩ ይገልጻሉ።
ዶክተር መሃሪን በአዲስ አበባ ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ነው።