በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕረዚዳንት ኦባማ የኬንያ ጉብኝት የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት እንደሚያጠናክር የኬንያው ፕረዚዳንት ገለጹ


Rais Kenyatta akihutubia taifa juu ya ziara ya Obama
Rais Kenyatta akihutubia taifa juu ya ziara ya Obama

የኬንያው ፕረዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ኬንያን በሚጎበኙበት ወቅት ከሚነጋገሩባቸው ነጥቦች መካከል አብይ ቦታ የሚይዙት ጸጥታና ንግድ እንደሆኑ ገልጸዋል። የኬንያው ፕረዚዳንት ለሀገሪቱ ባደረጉት ንግግር አለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በምክትላቸው ላይ ስለመሰረተው ክስም ሆነ ስለ ተመሳሳይ ጾታ ግንኑነት መብት ጉዳይ እንዳላነሱ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ጌብ ጃስሎ ከናይሮቢ በላከው ዘገባ ጠቅሷል አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ፕረዚዳንት ኬንያታ ትላንት ባደረጉት ንግግር ጸጥታና የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰት አብረው የሚሄዱ በመሆናቸው በፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት ወቅት ውይይት ይደርገባቸዋል ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ ኬንያ የሚሄዱት ከፕረዚዳንት ኬንያታ ጋር ሆነው የአለም አቀፉን የንግድ ስራ ጉባኤን ለመምራትና ከሀገሪቱ መሪዎች ጋር ለመነጋገር ነው።

አለም አቀፍ የወንጃል ችሎት በፕረዚዳንት ኬንያታና በምክትላቸወ ዊልያም ሩቶ ላይ በተመሰረተው ክስ ምክንያት የ United States እና የኬንያ ግንኙነት ሻክሮ ነበር። ሁለቱ መሪዎች እአአ በ 2007 አም ከተካሄደው ምርጫ በኋላ የተከሰተውን ግጭት በማስተባበር ተግባር ውስጥ እጃቸው አለበት በሚል መከሳሰቸው ይታወሳል።

ፕረዚዳንት ኬንያታ ታድያ የፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት በሁሉቱም ሀገሮች መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኑነት ያመለክታል ብለዋል።

“እንዲህ አይነቱ ጉባኤ ከሰሀራ በመለስ ባለው የአፍሪቃ ክፍል ሲደረግ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። የኬንያ ጉባኤውን ለማስተናገድ መመረጥ ሀገራችንና አስተዳደርዋ ላሳያየነው መሻስልና ላለን መሰረት እውቅና መስጠት ነው የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ" ብለዋል።

የኬንያ ፕረዚዳንት አያይዘውም በመሰረተ-ልማት ዝርጋታ፣ በጤና ጥበቃና በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚደረገው የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰት መጨመር ሀገሪቱን ይጠቅማል ብለዋል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

Kenya President Obama 7-22-15
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG