ፕረዚዳንት ኦባማ ወደ አፍሪቃ የሚጓዙት ባለፈው አመት በተከሄደው የ United States እና የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ላይ የታየውን መሻሽል ለማጠናከር ነው። ወደ ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ከማምራታቸው በፊት በኬንያ መዲና ናይሮቢ በመጪው ቅዳሜና እሁድ በአለም አቀፍ የንግድ ስራ ጉባኤ ይሳተፋሉ።
ፕረዚዳንቱ አዲስ አበባ መሄድ የለባቸውም ብለው የሚያያስቡ ሰዎች አሉና ለምን ይመስሎታል ለሚለው ጥያቄ በአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሊንዳስ ቶማስ ግሪንፊልድ ለኛ ጠቃሚ ጉብኝት ነው ሲሉ መልሰዋል። " የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በአሸባሪነት ላይ የሚያካሄዱትን ትግል በመደገፍ ረገድ ያለንን ቁርጠኛነት ያሳያል። ሰብአዊ መብትንና የፕረስ ነጻነትን በሚመለከት ለኢትዮጵያ መንግስት መልእክቶች ለማስተላላፍም ለፕረዚዳንቱ እድል ይከፍታል። ከሰብአዊ መብት አንጻር ኢትዮጵያ ትክክለኛውን ቦታ እንድትይዝ ይህ መንግስት ጥረት ማድረጉ ይቀጥላል" ብለዋል።
Jeffrey Smith የተባሉ የሮበርት ኬኔዲ የሰብአዊ መብት ማዕከል ቦርድ ሊቀ-መንበር ደግሞ “ኢትዮጵያ ዐል ሸባባን በመከላከል ረገድ ጽኑ አጋር ተደርጋ ትታያለች። ከክላላዊ ትብብር አንጻር ብቻ ሳይሆን በአህጉሪቱ ዙርያ ለአፍሪቅ ህብረት የሰላም ጥበቃ ተልእኮዎች ወታደሮች በማቅረብም ጭምር ነው። በተለይም በሱዳንና በደቡብ ሱዳን ላለው ቀውስ መፍትሄ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ያላት ሚናንና የሸምጋይነት ሚናውን በሚመለከት ኢትዮጵያ ዋናዋ አጋር ተደርጋ ትታያለች በማለት አስረድተዋል።
Smith አያያዘውም ኢትዮጵያ ጨቋኝ ሀገር በመሆንዋ የፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት የተሳሳተ መልእክት ያስተላልፋል ብለዋል። ኢትዮጵያ በአለም ከባድ ሳንሱር ከሚደረግባቸው ሀገሮች አራተኛዋ ናት። ጋዜጠኞችን በማሰር ረገድ ከመላ አህጉሪቱ ከኤርትራ ቀጥላ ትፈረጃለች ብለዋል። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።