በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


Axum-Lalibela
Axum-Lalibela

ኢትዮጵያ ለአመቱ ምርጥ የጎኝዎች መዳረሻነት ተመረጠች፣ የኢትዮጵያን የውሀ መሰረተ- ልማት ዘማናዊ ለማድረግ የ 81 ሚልዮን ይሮ ብድር እንደሚሰጣት ታወቀ፣ ከእስር የተፈታ ጋዜጣኛ እንደገና የመታሰር ስጋት እንዳለው ገለጸ የሚሉትን ርእሶች ነው ዛሬ የምንመለከተው ።

Daily Mail የተባለው በብሪታንያ የሚታተም ጋዜጣ ድረ-ገጽ ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የጎኝዎች መዳረሻ ተብላ እንደተመረጠች ገልጾ እንግዲህ አማርኛን ብታቀላጥፉ ይሻላል ሲል ለፈገግታ ያህል አስፍሯል። ለውድድር የቀረቡት ሀገሮች 31 ሲሆ፣ ኢዮጵያ ከሁሉም ልቃ አንደኛ ሆናለች።

የአውሮፓ የጉብኝትና የንግድ መማክርት ኢትዮጵያን የአመቱ ምርጥ የጎብኝዎች መስህብ ብሎ ሲሰይም በ UNESCO ማለትም በተባበሩት መንግስታ የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በአለም ቅርስነት የተመዘገቡትን ድንቅ ቅርሶች በመጥቀስ ማድነቁን Daily Mail ጠቅሷል። እጹብ ድንቅ የሆነ የተፈጥሮ ውበት ቀልብ የሚስብ መልከአ-ምድራዊ አቀማመጥና ጥንታዊ ባህሏን እንደ አብነት ጠቅሷል። አምና በጎብኝዎች መስሕብነት ምርጥ ተብላ የተሰየመችው ዚምባባዌ ነበረች።

የጎብኚዎች ፍሰት ለድህነት ቅነሳ ለአከባቢው ህብረተ-ሰብ እድገትና ለኢኮኖሚ ነጻነት የሚረዳ ፍቱን ስትራቴጂ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። ኢትዮጵያ በያዝነው አመት ከጎብኝዎች የሚገኘው ገቢ$3 ቢልዮን ዶላር እንዲደርስ የማድረግ እቅድ አላት። አቻ አምና ከጉብኝት የተገኘው ገቢ $2 ቢልዮን ዶላር እንደነበር Daily Mail ገልጾ እቅድዋ ከተሳካላት ኬንያንንና ታንዜንያን የመሳሰሉት በምስራቅ አፍሪቃ የበላይነት ቦታ ይዘው የቆዩትን ሃገሮች መገዳደር ትጀምራለች ይላል።

---------

ብሉምበርግ የዜና አገልግሎት ደግሞ የአውሮፓ የልማት ባንክ፣ ፈረንሳይና ኢጣልያ ኢትዮጵያ የውሀ መሰረተ-ልማትዋን ዘምናዊ ለማድረግ የሚያስችላት የ 81.4 ሚልዮን ይሮ ብድር ያቀርቡላታል። የአውሮፓ የልማት ባንክ 40 ሚልዮን ይሮ፣ የፈረንሳይ የልማት አግልግሎት 20 ሚልዮን፣ የኢጣልያ የውጭ ጉዳይና የለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ደግሞ 15 ሚልዮን ይሮ ለኢትዮጵያ ያብድራሉ። ተጨማሪ 6.4 ሚልዮን ይሮ በልገሳ መልክ እንደሚሰጣት የአውሮፓ የመዋዕለ-ነዋይ ባንክ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከአፍሪቃ እጅግ በላቀ ፍጥነት እያደገ መሆኑን የገለጸው የአውሮፓ የመዋዕለ-ነዋይ ባንክ ብድሩ የሚሰጠው በመላ ሀገሪቱ በሚገኙት አነስተኛና መካከለኛ ከተሞች ዘንድ ያለውናን የውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ዘማናዊ ለማድረግ እንደሆነ መግለጹን፣ ብሉምበርግ የዜና አገልግሎት ጠቁሟል። ሌሎች ርእሶችንም አካተናል። ሙሉዉን ዝግጅት ያድምጡ።

አፍሪካ በጋዜጦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG