በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳምንታዊ የስፖርት ዜና


ካናዳ ያስተናገደችው የ 2015 የሴቶቹ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በዩናይትድ ስቴትስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። አምበሏ Carli Lloyd ከግማሽ ሜዳ መትታ ያገባችውን ጨምሮ በጠቅላላው ሦስት ጎሎችን በማስቆጠር ታሪክ ሠርታለች።

እስከዛሬ በተደረጉ የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ከሁለት ጎል በላይ ያገባ ቲም የለም። Lloyd ግን አንድ አክላበት በጠቅላላው በ 13 ደቂቃዎች ሦስቱን አግብታ በእኣለም ተደናቂ ሆናለች። ጠቅላላው ውጤት፥ ዩናይትድ ስቴትስ 5 ጃፓን 2

32ኛው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ዓመታዊ ፌስቲቫል፥ በድምቀት ተጀምሮ በድምቀት አብቅቷል። ለአንድ ሳምንት በቆየው የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ የተገኙት፥ የዓለምአቀፍ ስፖርት ተቋማቱ ልዩ አማካሪ ፍቅሩ ኪዳኔ የማጠቃለያ አስተያየት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያውያን በያመቱ የሚሰባሰቡበት ፕሮግራም በመሆኑ ሊበረታታና ሊታገዝ የሚገባው ነው ብለዋል።

በአትሌቲክስ፥ ገንዘቤ ዲባባና አልማዝ አያና በፓሪሱ የዳያመንድ ሊግ 5000 ሜትር ሩጫ ውድድር አሸነፉ።

ስፖርት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG