በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


Wind farms
Wind farms

ኢትዮጵያ በ 10 አምታታ ውስጥ ሳተላይት የማምጠቅ እቅድ እንዳላት ተገለጸ፣ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኤነርጂ ማትኮርዋ ታወቀ፣ የአፍሪቃ ደካማ የመብራት ሃይል አቅርቦት ኢኮኖሚዋን እያጫጨ ህዝቡንም እያበሳጨ እንደሆነ ተገለጽ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው አፍሪቃ በጋዜጦች ዝግጅታችን የምናቀርበው።

Turkishweekly የተባለው በቱርክ የሚወጣ ድረ-ገጽ ኢትዮጵያ እአአ በ 2025 አም (ከ 10 አመታት በኋላ ማለት ነው) ከአለም አቀፍ የጠረፍ ጣብያ ጋር የመቀላቀል እቅድ አላት በሚል ርእስ ባቀረበው ጽሁፍ የኢትዮጵያ መንግስት በጠፈራ ሳይንስ ምርምርና በልማት የሚመደበውን መዋዕለ ነዋይ ከፍ እያደረገ ነው ይላል።

በኢትዮጵያ የመጀመርያው የጠፈር ምርምር ማዕከል እስከ 2025 አም ባለው ጊዜ በአስር አመታት ውስጥ ማለት ነው ሳተላይት ለማምጠቅ ሲዘገጅ እንደቆየ ገልጿል።

ማዕከሉን ከሶስት አመታት በፊት እንጦጦ ተረራ ላይ የመሰረተው የኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ ማህበር እንደሆነ Turkis hweekly የተባለው ድረ-ገጽ ዘግቧል።

--------

የኢትዮጵያው የጠፈር ማህበር ከ 11 አመታት በፊት የተመሰረተው ከተለያዩ የሳይንሳ ዘርፎች በተሰባሰቡ ወዶ-ገቦች እንደሆነ አላማውም ስለጠፈርና ስለሳይንስ ጉዳዮች ህዝብን ለማንቃት እንደሆነ ድረ-ገጹ በዘገባው ጠቅሷል።

Gulf Times የተባለ በቓታር የሚታተም እለታዊ ጋዜጣ ድረ-ገጽ በበኩሉ አዳማ ስላለው የነፋስ መብራት ሃይል ማመንጫ ጣብያ ሲዘገብ አዳማ የሚገኙት አለታማ ኮረብታዎች ነፋስ በሚባዛባት አከባቢ ከአህጉሪቱ ግዙፍ ከሚባሉት የነፋስ የመብራት ሃይል ማማንጫ ቦታዮች መሆናቸውን ይገልጻል።

ባለፈው ወር በአዳማ የተጀመረው በነፋስ የኤለክትሪክ ሃይል ማመንጫ ተቋም የ 153 ሜጋዋት የመብራት ሀይል የማንጨት ብቃት አለው። ይህም ከሰሀራ በመለስ ካሉት በነፋሰ የመብራት ሃይል ማመንጫ ጣብያዎች ግዙፉ እንዲሆን ኢትዮጵይ ካሉት ሶስት ግዙፍ የነፋስ ማመንጫ ሃይሎችም አንዱና አዲሱ ያደርገዋል ሲል፣ Gulf Times ድረ ገጽ ጠቁሟል።

--------

የ New York Times ጋዜጣ ድረ-ገጽ ደግሞ በአፍሪቃ ያለው የኤለክትሪክ መብራት ማሰራጫ መረብ ድክመት የአህጉርዋን ኢኮኖሚ እያጫጨ ህዝቡንም እያበሳጨ ነው ሲል ባቀረበው ጽሁፍ ከሰሃራ በመለስ ያሉት የአፍሪቃ ሀገሮች አጠቃላይ የመብራት ሃይል ማመንጫ አቅም ከደቡብ ኮርያ ያነሰ ነው። ካለው የአፍሪቃ የመብራት ሃይል ማመንጫ መጠንም በመሰረተ-ልማቶች መቆርቆዝ ምክንያት አንድ አራተኛው አይሰራም ይላል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

አፍሪካ በጋዜጦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:17 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG