በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ ስልጣን በአንድ ሰውና በአንድ ፓርቲ መዳፍ የተጨበጠ ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኮምሽን ዘገባ ገለጸ


Eritrean President Isaias Afeworki
Eritrean President Isaias Afeworki

በኤርትራ ይፈጽማል ስለሚባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከታትሎ ጥናት እንዲያቀርብ ባለፈው አመት መስከረም ወር ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተሰየመው ኮሚሽን ዘገባውን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ካውንስል ባለፈው ማክሰኞ አቅርቧል። ሁኔታውን ለማሻሳል አስፈላጊ ያለውን ምክረ-ሃሳብንም አቅርቧል። ዝርዝር ዘገባውን አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ካውንስል ፕረዚዳንት Joachim Rucker የኮሚሽኑን ስብሰባ ሲከፍቱ ዘገባውን ባቀረበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኮሚሽን አባላት ላይ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰ ጠቁመዋል።

“የኮሚሽኑ አባላት ጄኔቫ እንደገቡ በሆቴላቸውና በመንገዶች ላይ የተለያዩ የማስፈራራት ተግባሮችና ዛቻዎች እንደደረሰባቸው ልገልጽላችሁ እወዳልሁ። ለኮሚሽኑ አባለት የሚደረገው የጸጥታ ጥበቃ በእጥፍ እንዲጨምር ተደርጓል። ልዩነቶች ካሉ በሚገባ ሊገልጹ ይችላሉ። ሆኖም የኮሚሽኑ አባላት ለዛቻና ለማስፈራርት ተግባር ሊዳረጉ አይገባም። የሰብአዊው መብት ካውንስል ፕረዚዳንት እንደመሆኔ መጠን ይህንና ተያያዥ ጉዳዮችን በቢሮው ደረጃ እከታተለዋለሁ” ብለዋል Rucker።

የሰብአዊው መብት ካውንስል ፕረዚዳንት ይህን ካሉ በኋላ የኤርትራን የሰብአዊ መብት አይያዝ ጉዳይን እንዲያጠና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተሰየመው ኮሚሽን ሊቀመንበር ማይክ ስሚት በኤርትራ ስላለው ሁኒታ የሚገልጸውን ዘገባ አቅርበዋል።

“ኤርትራ ነጻ ከወጣች ከሁለት አስርተ-አመታት በላይ አልፏል። ለመላ ህዝቧ ነጻነትና የብልጽግና መጻኢ ሁኔታ እንዲኖር ነበር የተጠበቀው። ሆኖም ይህ ተስፋ በተግባር ላይ ሊውል አልቻለም። በአሁኑ ወቅት የዲሞክራስያዊት ኤርትራና የሰብአዊ መብት ረገጣ የሌለባት ኤርትራ ህልም ከምን ጊዜ የራቀ ይመስላል። የአሁኗ ኤርትራ በጭቆናና በፍርሀት ተሽብባለች። ከነጻነት በኋላ የኤርትራ ስልጣን በአንድ ሰውና በአንድ ፓርቲ መዳፍ የተጨበጠ ሆኗል ሲሉ ስሚት ባቀረቡት ዘገባ ተናግረዋል።

የኤርትራው ተወካይ አምባሳደር ተስፋ ሚካኤል ገራህቱ በበኩላቸው ለኮሚሽኑ ዘገባ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ማዕቀቡ በወጣትዋና አነስተኛዋ ሃገር ትልቅ የኢኮኖሚና የልማት ጉዳት አድርሷል። ይህ ሁሉ ከመጀመርያውኑ ኤርትራን በማዋከቡ ተግባር ለመቀጠል የተጠነሰስ የፖለቲካ ደባ መሆኑን ማስረጃው ያሳያል" ብለዋል።

አምባሳደሩ ቀጥለውም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኮሚሽን የ 550 ጥገኝነት ጠያቂ ምስክርነትና 150 በጽሁፍ የቀረቡ መረጃዎችን ይጠቅሳል። በመጀመርያ ደረጃ በዳያስስፖራ ያሉት ኤርትራውያን ወደ አንደ ሚልዮን የሚጠጉ በመሆናቸው ይህ ተገቢ ምስክርነት ሊሆን አይችልም ሲሉ አስገንዝበዋል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG