በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የወደፊት እጣ


ዶ/ር መረራ ጉዲና
ዶ/ር መረራ ጉዲና

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሀገሪቱ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ የኢህአዴግን አገዛዝ ሊሰብሩ ወይም በምክር ቤቱ መቀመጫዎች ለማግኘት አልቻሉም። ስለሆነም ለ 24 አመታት ያህል ተገለው የቆዩት ተቃዋሚዎች በፖለቲካው መድረክ አማራጮች ይኖርዋቸው ይሆን? የሚል ጥያቄ ያቀረበችው ዘጋብያችን ማርት ባን ደር ዎልፍ የተቃዋሚ መሪዎችን አነጋግራ ከዲስ አበባ የላከችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው ብሄራዎ ምርጫ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወከባና ማስፈራራት ይደርስብናል ምርጫውም ተጭበርብሯል የሚል ክስ ሲያሰሙ ቆይተዋል። ገዢው ፓርቲ መላ የምክር ቤት መቀመጫዎችን በማሸነፍ ለሌላ አምስት አመታት በስልጠን የመቆየትቱ ጉዳይ አይቀርየ ይመስላላ።

ተቃዋሚው የኢትዮጵያ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ የምርጫው ሂደት ፍትሀዊ አይደለም። የምርጫው ውጤትም ተአማኒነት የለውም ይላል። የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ዋሲሁን ተስፋየ በወቅቱ መድብለ-ፓርቲ ስርአት አጣብቂኝ ውስጥ ተገብቷል። ይሁንና ተቃዋሚ ሀይሎች ይቀጥላሉ ብለዋል።

“ከ 24 አመታታ በኋላ ተቃዋሚው ወገን ብዙ ተግዳሮቶች ገጥመውታል። ይሁንና አሁንም ህልውናው አለ። ቀጣዮቹ አምስትና አስር አመታት በተቃዋሚዎች ላይ አደጋ ይደቀናሉ”ብለኣል አቶዋሲሁን።

ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እድገትዋ ስትመሰገን በሰብአዊ መብት አያያዝዋ ግን ትነቀፋለች። 57 የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለፈው ወር በተካሄደው ሄራዊ ምርጫው ተሳትፈዋል። ይሁንና በመንግስቱ ላይ ውጊያ የሚያካሄዱ የታጠቁ ቡድኖችም አሉ።

የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ ሊቀ-መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናም ሰላማዊ ትግል ካልሰራ ሌሎች ሀይሎች በፖለቲካው አድማስ የባለይነት ሊያገኙ ይችላሉ ማለታቸውን ማርት በዘገባዋ ጠቅሳለች። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG