በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ጆሐንስበርግ ከተማ ላይ በቅርቡ ስብሰባ ባካሄዱበት ወቅት፥ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ተወያይተዋል። ባለሥልጣኗ በዚህ ቃለ ምልልስ፥ የመሪዎቹን ጉባዔ ባብዛኛው ባነጋገሩ አራት ነጥቦች ላይ አትኩረዋል።
ነጥቦቹም አጨቃጫቂው የሱዳኑ ፕሬዘዳንት አል ባሺረመሪዎቹ ጉባዔ ላይ መገኘት፥ ሁለተኛው በደቡብ ሱዳን የቀጠለው የርስ በርስ ውጊያ፥ ሦስተኛው፥ የቡሩንዲው የፖለቲካ ቀውስ እና አራተኛው የአፍሪካ መሪዎች ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርጉት ሕገ-ወጥ አካሄድ የሚሉ ናቸው።
ባለሥልጣኗ በነዚህ ነጥቦች ላይ የሰጧቸውን አስተያየቶች ከውይይቱ ያድምጡ።