በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰማያዊ ፓርቲ መሥራች አባል ጎጃም ውስጥ ተገደለ!


ሰማያዊ ፓርቲ
ሰማያዊ ፓርቲ

በግንቦት 16ቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ፥ ተቃዋሚውን የሰማያዊ ፓርቲ በመወከል በምሥራቅ ጎጃም ዞን ለደብረማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወዳዳሪየነበረው አቶ ሣሙኤል አወቀ ዓለም፥ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ማታ ተገድሎ መገኘቱን ፓርቲው አስታወቀ።

አቶ ሣሙኤል ቀደም ሲል በምርጫው ዘመቻ ወቅት የግድያ ማስፈራሪያ ከደህንነት ሠራተኞች ይደርሰው እንደነበር በፌስቡክ አማካይነት ባሠራጨው መልዕክትመግለጹ ታውቋል።

አቶ ሣሙኤል ተደብድቦ መሞቱን በእጄ የሚገኝ ሃኪም የፈረመበት ሪፖርት ቅጂ ያረጋግጣል ሲሉ በጎጃም የሰማያዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አሻግሬ ታምር-ገብሬተናግረዋል።

ፖሊስ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉም ታውቋል።

የመንግሥቱ ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው ለሮይተርስ የዜና ወኪል በሰጡት ቃል፥ በአቶ ሣሙኤል ላይ ጥቃቱን ያደረሰው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሏል፥ሌላው ተባባሪው እየታደነ ነው። ጉዳዩን ግን ምንም ከፖለቲካ ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም ብለዋል።

XS
SM
MD
LG