በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


Harar, Jogol
Harar, Jogol

አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። አዲስ አበባ አከባቢ ግዙፍ አይሮፕላን ማረፍያ እንደሚሰራ ታወቀ፣ ሀረር ጊዜ የማይሽራት ከተማ እንደሆች ተዘገበ፣ ኢቦላ እያሽቆለቆል እንደሄደ ተገለጸ የሚሉትን ርእሶች ነው ዛሬ የምንመለከተው።

Taipei Times የተባለው የታይዋን ጋዜጣ ድረ-ገጽ ኢትዮጵያ ከአዲስ አባባ ወጣ ባለ ቦታ ላይ ልትሰራው ያቀደችው ትልቅ አይሮፕላን ማረፍያ ተግባራዊ ለመሆን ገና ብዙ አመታት ቢቀሩትም በጣም ትልቅ እንደሚሆን የኢትዮጵያ አይሮፕላን ማረፍያዎች ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴድሮስ ዳዊት መናገራቸውን ጠቅሷል።

“ለመስራት ያቀድነው አይሮፕላን ማረፍያ ግዙፍ በጣም ግዙፍ ይሆናል። በአለም ደረጃ ካሉት ትልልቅ አይሮፕላን ማረፍያዎች አንዱ ይሆናል" ሲሉ አቶ ቴድሮስ ዳዊት መግለጻቸውን ድረ-ገጹ ጠቁሟል።

ሊገነባ የታቀደው አይሮፕላን ማረፍያ የኢትዮጵያ መንግስት ካቀዳቸው የመሰረተ-ልማት ዝርጋታዎች አንዱ ሲሆን ይህች የምስራቅ አፍሪቃ ሀገር እያደገች ያለች የአፍሪቅ ግዙፍ ሀይል የሚል ስያሜ እያገኘች ነው ይልል የ Taipei Times ድረ-ገጽ።

በአስር አመታት ጊዜ ውስጥ በብዙ ቢልዮን ዶላሮች ወጪ እንዲገነባ የታቀደው አዲስ አይሮፕላን ማረፍያ የሚሰራው በቦሌ አለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ ላይ እየበዛ የሄደውን የትራፊክ ብዛት ለማቅለል ነው። ከአስር አመታት በፊት ከታየው የ 900,000 ተሳፋሪዎች ብዛት ባለፈው አመት ከ 7 ሚልዮን በላይ ወደ ሚሆኑ ተሳፋሪዎች እንዳደገ ዘገባው ያወሳል።

ከአፍሪቃ ትልቁና ለሀገሪቱ ከፍተኛ ትርፊ የሚያስገኝ ዘርፍ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያበበ በሄደው የአፍሪቃና እስያ ገበያ ላይ በማትኮር እያደገና እየሰፋ እንደሄደ Taipei Times ዘግቧል።

CNN በሚል አህጽሮተ-ቃል የሚታወቀው Cable News Network ድረ ገጽ ደግሞ በጥንታዊ ግንብ ስለታጠረችው ሃረር ከተማ ጽሁፍ አቅርቧል። ጽሁፉን ያቀረበው የ CNN ዘጋቢ Jemes Jeffrey የማትረሳ ስላላት ሀረር ከተማ ሲጽፍ ጠባቦቹ ውስብስብ መንገዶችዋ፣ የሚያውደው የገበያዎቹ መአዛ፣ ጭንቅላታቸው ላይ ስፌት ተሸክመው የሚራመዱት ቆነጃጂት፣ሙስሊሞች የሚያደርጉት የጸሎት ጥሪ ድምጽ እነዚህ ሁሉ ከአስራ አንድ አመታት በፊት ሀረርን ለመጀመርያ ጊዜ ከጎበኘሁበት ጊዜ አንስቶ በአዕምሮየ ተቀርጸው ቀርተዋል ይላል ጋዜጠኛ ጀፍሪ።

በሀረር ጉዳይ የተመሰጥኩት እኔ ብቻ አይደለሁም። እአአ በ 2006 አም (ከዘጠኝ አመታት በፊት ማለት ነው።) ሀረር ከተማ በ UNESCO ማለት በተባበሩት መንግስታት፣ የትምህርት፣ የሳይንስና፣ የባህል ድርጅት በቅርስነት ተመዝግባለች ይላል የ CNN ኑ ዘጋቢ።

የ NBC News ድረ-ገጽም ስለኢቦላ በሽተኞች ቁጥር በጣም እየቀነሰ መሄድ ዘግቧል። ሙሉዉን ዝግጅት ያድምጡ።

Africa Press Review 4-10-15
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG