በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


አፍሪቃ የአለም አቀፍ ስለላ ትኩረት እንደሳበች ሾልከው የወጡ ሰነዶች ማመልከታቸው ተገለጸ፣ በህብረት ስራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የቁልቋል ማርማሌት አውሮፓ ለመላክ ተዘጋጁ፣ ኢትዮጵያ ነጻ ፕረስ እንደሚያስፈልጋት አንድ ደብዳቤ ገለጸ የሚሉትን ዘገቦዝ እናቀርባለን።

አፍሪቃ አዲስዋ የስለላ መናኸርያ እንደሆነች ሾልከው የወጡ የስለላ ሰነዶች ማመልከታቸውን የጋርዲያን ጋዜጣ ድረ-ገጽ ጠቁሟል። ጋዜጣው በተመለከተው ሚስጥራዊ የስለላ ሰነዶች መሰረት አፍሪቃ በደቡብ አፍሪቃ በር ከፋችነት የ 21 ኛው ምዕተ-አመት የሰለላ መናኸርያ ሆናለች ይላል። “አፍሪቃ በአሁኑ ወቅት የስለላ El Dorado ማለት የስለላ ሀብትየሚታፈስባት አህጉር ሆናለች” ሲል አንድ የውጭ ሀገር የስለላ መኮንን እንደተናገረ ጋርዲያን ድረ-ገጽ ጨምሮ ገልጿል።

ቻይና በአፍሪቃ ላይ ያላት የኢኮኖሚ ሚና እያደገ በሄደበት United States እና ሌሎች የምዕራብ ሀገሮች በአፍሪቃ ላይ በሚካሄደው አዲስ አለም አቀፍ ትግል መሰረት ወታደራዊ ህልውናቸውን እያሰፉ በሄዱበትና በተፈጥሮ ሀብቷ ላይ የሚካሄደው ቅርምት በተጧጧፈበት በአሁኑ ወቅት አህጉሪቱ የአለም አቀፍ የስለላ ትኩረት እየሳበች እንደሆነ ድረ- ገጹ አውስቷል።

ደቡብ አፍሪቃ የአከባቢው ዋና አንቀሳቃሽ ሃይልና የኮሙኒኬሽንስ ማዕከል በመሆንዋ የአህጉሪቱ የስለላ ማዕከልና የአለም አቀፍ የስለላ ኢላማ ሆናለች ሲሉ የሰለላ ባለስልጣኖች መናገራቸውን ድረ-ገፁ አውስቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዜና ማዕከል ደግሞ የኢትዮጵያ ከቁልቋል የተሰራ ማርማሌድ ኢጣልያ ውስጥ Eataly በተባለ ምርጥ ምግቦች በሚሸጡበት የምግብ መደብር እንደሚቀርብ ጠቁሟል።

FAO በሚል አህጽሮተ-ቃል የሚታወቀው የተባበሩት መግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት Eataly ከተባለው የኢጣልያ የምግብ መደብር ጋር በመተባበር በአለም ደረጃ ያሉትን አርሶ አደሮች ለመርዳት በሚያደርጉት ጥረት አንድ በህብረት ስራ የተሰማራ የኢትዮጵያ ሴቶች ቡድን 4,000 ጠረሙስ የሚሆን ከቁልቋል የተሰራ ማርማሌት ወደ ኢጣልያ ለመላክ ዝድጁ መሆኑን ገልጿል። ስለ ፕረስ ነጻነት የተጻፈ ድብዳቤም አለን። ዝርዝሩን ያድምጡ።

Africa Press review -2-27-15
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:32 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG