በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሦ ጊዳዳ በዩናይትድ ስቴትስ National Endowment For Democracy ተቋም ጥናታዊ ጽሑፍ ኣቀረቡ


Negaso Gidada
Negaso Gidada

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሦ ጊዳዳ ትላንት እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ The National Endowment For Democracy የተባለው ዓለምአቀፍ የጥናት ተቋም ባመቻቸላቸው መድረክ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

ዶክተር ነጋሦ ባቀረቡት በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ያተኮሩት እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር “ሕገ-መንግሥቱ የሁሉንም ብሄረሰቦች ፍላጎት ማንፀባረቅ ያስፈልገዋል” በሚለው ላይ ነው።

በኢትዮጵያ የፊታችን ግንቦት ስለሚካሄደው ምርጫ፥ በሀገሪቱ ስለታየው የረዝም ጊዜ መረጋጋትና ልማትም በጽሁፋቸው ዳሰዋል።

ዶክተር ነጋሦ እ አ አ ከ 1995 እስከ 2001 ዓም ድረስ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት፥ ከ 2005 እስከ 2010 ደግሞ የፓርላማ አባል፥ አሁን በቅርቡ ደግሞ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትሕ ፓርቲ ሊቀ መንበር ሆነው ከ 2012 እስከ 2013 ዓም ድረስ ለአንድ ዓመት ሠርተዋል። በ 1994 የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት በማርቀቅ የተሳተፉ ሲሆን በ 1995 የፈረሙትም እርሣቸው ናቸው።

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG