ገንዘቤ ዲባባ በአዳራሽ ውስጥ 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች።
እንግሊዛዊ Mo Farah ላለፉት ሰባት ዓመታት በቀነኒሣ በቀለ ተይዞ የቆየውን የሁለት ማየል የቤት ውስጥ ሬኮርድ ሠበረ።
በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ፆታዎች ድል ተቀዳጅተዋል። በዘጠኝ ዓመቱ የቦታው ውድድር ታሪክ ከአንድ ሀገር የመጡ የሁለቱም ፆታዎች አትሌቶች ሲያሸንፉ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።