በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


coffee in ethiopia
coffee in ethiopia

ጥላ የሚበዛባቸው የኢትዮጵያ የቡና ተክሎች ለአዕዋፍ ብዝሀነት እንደሚያመቹ ተገለጸ፣ በአመት 60 ቢልዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ በድብቅ ከአፍሪቃ እንምደሚወጣ ታወቀ፣ የአፍሪቃ ወጣት ነጋዴዎች የአህጉሪቱን ገጽታ እንደሚቀይሩ ተዘገበ የሚሉትን ርእሶች ነው ዛሬ የምናቀርበው።

ጥላ የሚበዛባቸው የኢትዮጵያ የቡና ተክሎች በአለም ዙርያ ካሉት የቡና ተክሎች የበለጡ የአዕዋፍ አይነቶች እንደሚገኙባቸው አንድ አዲስ ጥናት ማመልከቱን nationalgeographic የተባለው መጽሄት ድረ ገጽ ጠቁሟል።

አዲሱ ጥናት እንደሚለው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ባህላዊ የቡና አበቃቀል ዘዴ በአለም ዙርያ ካሉት የቡና እርሻዎች ይልቅ ለአዕዋፍ ብዘሀነት ያመቻል።

አፍሪቃ ያሉ ኩባንያዎችና የመንግስት ባለስልጥኖች በየአመቱ 60 ቢልዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ከአህጉሪቱ እንደሚያስወጡ የ Wall Street Journal ጋዜጣ ድረ-ገጽ አንድ ባለፈው እሁድ የወጣ ዘገባን ጠቅሶ ዘግቧል። ይህ ተግባርም ከአለም ድሀ በሆነችው አህጉር የኢኮኖሚዋን እድገት በማፋጠን ላይ ሊውል የነበረውን ገነዝብና የግብር ገቢን እንደሚያሳጣ ድረ-ገጹ ያወሳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪቃ ህብረት የሚያንቀሳቅሱት በቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕረዚዳንት ታቦ እምቤኪ የሚመራ ቡድን ያቀረበው ዘገባ አንዳንድ ኩባንያዎች ገንዘብ ከሀገሪቱ በድብቅ ለማስወጣት ስለሚጠቀሙት ዘዴ ይገልጻል። ገነዘቡ ከአፍሪቃ ወደ ውጭ መውጣቱ የሚያደርሰው ከባድ ጉዳት በገቢነት ደረጃ ብቻ ሳይሆን ከልማት አንጻርም ጭምር እንደሆነ ታቦ እምቤኪ መግለጻቸውን ድረ-ገጹ ጠቁሟል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:06 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG