የአለም ባንክ ድረ-ገጽ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብት ለሀገሪቱ እድገትና ትራንስፎሜሽን እቅድ ትልቅ አስተዋጾ የማድረግ መሰረት ያለው ቢሆንም ለዛ እንዳልበቃ ይጠቅሳል።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ካለፈው አስርተ-አመት ወዲህ በአመካኝ በ 10.7 ከመቶ ሲራመድ ቆይቷል። ከሌሎች ከሰህራ በመለስ ያሉት የአፍሪቃ ሀገሮች የእድገት ደረጃ ከእጥፍ በላይ በሆነ መጠን እያደገ ነው። የሌሎቹ የአፍሪቃ ሃገሮች እድገት በ 5.2 ከመቶ ደረጃ ነው የነበረው። ይሁንና ለኢኮኖሚው እድገት በበለጠ አስተዋጽኦ ሊያደርግ የሚችለው የነዳጅ ዘይት፣ የጋዝና ሌሎች እምቅ የሀገሪቱ ሀብቶች የኢኮኖሚው እድገት አንቀሳቃሽ ሀይል ሊሆኑ አልቻለም ይላል የአለም ባንኩ ድረ-ገጽ።
የኢትዮጵያ መንግስት ለነዳጅ ዘይትና ለተፈጥሮ ጋዝ እሰሳ እንዲሁም ለማዕድን ኢንዱስትሪ የሚያስፈልግ ህጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ በማውጣት ብቃት ያለውና ተአማኒ እንዲሁም ተገቢ ስትራቴጂ ለመቀየስ እንዲችል የአለም ባንክ ቡድን ቴክኒካዊ እርዳታ እያደረገለት ነው ሲል የአለም ባንኩ ድረ-ገጽ ዘግቧል።
The Guardian ጋዜጣ ድረ-ገጽ ደግሞ በቀጣዮቹ 15 አመታተ ውስጥ ቴክኖሎጂ በአፍሪቃ ላይ ስለሚኖረው ቦታ ሲዘግብ የ CIA ማለት የ United States ማዕከላዊ የስለላ አገልግሎት ከ 15 አመታት በፊት አውጥቶት የነብረውን ትንበያ የሚጻራሪ እንደሆነ ይገልጻል።
እአአ በ 2000 አም የወጣው የ CIA ዘገባ ቀቢጸ-ተስፋነት የሚያንጸባርቅ እንደነበር ድረ-ገጹ ያወሳል። ከሰሀራ በመለስ ያሉት የአፍሪቃ ሀገሮች ለአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ብዙም ጥቅም አይኖራቸውም፣ በቀጣዮቹ 15 አመታት ውስጥ (አሁን በደረስንበት ደረጃ ማለት ነው።) የአፍሪቃ ዲሞክራሲ ሊደርስ የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ አብቅቶለታል፣ የቴክኖሎጂ እድገትም፣ በአፍሪቃ ኢኮኖሚዎች ላይ፣ ብዙም አዎንታዊ ተጽእኖ አይኖረውም የሚል እንደነበር ጽር-ገጹ ጠቁሟል። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።