The guardian ጋዜጣ ድረ-ገጽ ጋምቤላ ስላለው ሰፊ የንግድ እርሻ እቅድ ባሰፈረው ጽሁፍ እቅዱ ችግር እየገጠመው እንደሆነና የአከባቢው ማህበረሰብ ብዙም እንዳልተጠቀመ ይጠቅሳል።
BHO Bioproducts የተባለ የ Anglo-Indian ኩባንያ በጋምቤላ በተከራየው የ 27,000 ሄክታር መሬት ሩዝና ጥጥ ያበቅላል። ጃኮብ ፖች የተባሉ ንዌር ወንጌላዊ ሰባኪ ኩባንያው ለመንደሩ ነዋሪዎች ደንታ የለውም ይላሉ። የግጦሽ መሬት ከመታጣቱም በላይ የአከባቢው ነዋሪ ህዝብ እንዳይጠቀምበት ሲል የውሀ ቧምቧ ያለበትን ቦታ በእንጨት እንዳጠረው ይናገራሉ።
በአከባቢው ያሉት ቦታዎች ጋምቤላውያን ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን የመዋእለነዋይ መሬት መስጠቱ እንደሚያሳስባቸው አንድ አዛውንት እንደተናገሩ The guardian ድረ-ገጽ ዘግቧል።
አንድ ስማቸውን ያልገለጹ በእርሻ ስራ የተሰማሩ ደገኛ ግን መዋዕለ-ነዋይ አፍሳሾች ወደ አከባቢው ከመምጣታቸው በፊት የአከባቢው ነዋሪዎች ወንዝ ዳር ተቀምጠው ነበር የሚውሉት። መዋዕለ-ነዋይ አፍሳሾች መምጣት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ግን ኑሯቸው ተለውጧል። ኦፔረተሮችና ቴክኒሻኖች ሆነው እየሰሩ ነው። ለሰራተኞቹ በቀን 50 ብር እከፍላለሁ። ይህም በሀገሪቱ ደረጃ ከፍተኛ ነው። ለሰራተኞቹ የመጓጓዣ አገልግሎት አቀርባለሁ። ስምንት ቤቶች ለአስተማሪዎች መኖርያ ተሰርተዋል። 25 ሄክታር መሬት ለአከባቢው ነዋሪዎች እርሻ ተስጥቷል ማለታቸውን The guardian ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ያትታል። ሙሉውን ቅንብር ያድምጡ።