በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምርጫ ሂደት በኢትዮጵያ


ግርማ ሞገስ
ግርማ ሞገስ

ዲሞክራሲ በሰረጸባቸው ሀገሮች ምርጫ የዲሞክራሲ ወይንም የመብት መገለጫ መሳርያ እንደሆነ ዲሞክራሲ ባልሰረጸባቸው ሃገሮች ደግሞ ምርጫ የዲሞክራሲ ማምጫ ዘዴ መሆኑን አቶ ግርማ ሞገስ በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው ምርጫ ዝግጅት እንደተጀመረ የሚታወቅ ነው። ዲሞክራሲ በሰረጸባቸው ሀገሮች ምርጫ የዲሞክራሲ ወይንም የመብት መገለጫ መሳርያ እንደሆነ ዲሞክራሲ ባልሰረጸባቸው ሃገሮች ደግሞ ምርጫ የዲሞክራሲ ማምጫ ዘዴ መሆኑን አቶ ግርማ ሞገስ ባደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ አስገንዝበዋል።

አቶ ግርማ በሙያ የኤለክትሪካል ኢንጂኔር ሲሆኑ ስለ ሰላማዊ ትግል መጽሀፍ ጽፈዋል። ስለ ምርጫ አካሄድም ብዙ ጽፈዋል። አቶ ግርማን ያነጋገረችው አዳነች ፍሰሀየ ናት።

አቶ ግርማ ሞገስ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ምርጭ ምን መልክ መያዝ እንዳለበት ሲያስገነዝቡ በመንግስትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል መደረግ አለባቸው ያልዋቸውን ነጥቦች ዘርዝረዋል።

መንግስት ለተቃዋሚዎች የሚድያ ሰአት እንዲሰጥ፣ በእጩዎች ላይ የሚደረጉ ወከባዎችም እንዲቆሙ አቶ ግርማ ከጠቀስዋቸው ነጥቦች መካከል ናቸው።

በታቃዋሚዎች በኩል ደግሞ መደረግ አለባቸው ካልዋቸው ነጥቦች መካከል በሀገሪቱ ያለውን የመሬት ዋጋ መናር፣ የሙስና ጉዳይና በሀብታምና በደሀው መካከል ያለው የኑሮ ክፍተት በከፍተኛ ደረጃ መስፋትን በማንሳት እነሱ የተሻለ ሊሰሩ እንምደሚችሉ ህዝቡን በማሳመን ድምጽ እንዲሰጣቸው ለማድረግ እንደሚችሉ መክረዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:13:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG