በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሄራዊውን ምርጫ የቀለም አብዮት ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰሱ።


ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

ኒዮሊበራል ሀይሎች በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ምርጫ ከ 10 አመታት በፊት እንደሞከሩት ሁሉ የቀለም አብዮት ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሰሱ።

ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከውጭ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባኤ ነው ኒዮሊበራል ሀይሎች ያልዋቸውን ምርጫውን የቀለም አብዮት ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ የከሰሱት።

"ገዢው ፓርቲ ለሚቀጥለው አገር አቀፍ ምርጫ ዘመቻውን የሚያከናውነው እንደሚባለው ካሉት የንግድ ተቋማት ሳይሆን ከግል ባለሀብቶችና ከአባላቱ በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

በገዢው ፓርቲ አመራር ውስጥ ልዩነት አለ ስለሚባለው ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ ደግሞ በአመራሩ መካከል የሀሳብ አንድነት እንጂ ልዩነት የለም ብለዋል።

የግብጽ ፕረዚዳንት ኢትዮያን ለመጎብኘት ጠይቀው ኢትዮጵያ አልተቀበለችውም ተብሏል የሚለውን ከጋዜጠኞች የቀረበውን ነጠብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተባብለዋል።

"በመጀመርያ ደረጃ ግብጽ ወዳጅ ሃገር ናት። በአሁኑ ወቅት በጣም ጥሩ የሚባል ግንኙነት ነው ያለን። የግብጽ ፕረዚዳንት ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ የማንፈቅድበት አንድም ምክንያት የለም። እንደሚመስለኝ ጥያቄው ቀርቧል። እኛም አዎንታዊ ምላሽ ሰጠናል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ለጋዜጠኞች ጥያቄ ምላሽ ከሰጡባቸው ነጥቦች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። ዝርዝሩን ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG