ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን የጤን ሰራተኞች ከ 300 በላይ የሚሆኑ የጤና ሰራተኞችን ህይወት ባጠፋው የኢቦላ ህክምና ተግባር ለመርዳት ምዕራብ አፍሪቃ እንደገቡ Aljazeera የተባለው የቴሌቪዥን የዜና ስርጭት ዘግቧል። በያዝነው ወር ብቻ ሲየራ ልዮን ውስጥ ሁለት ዶክተሮች በአንድ ቀን በኢቦላ ምክንያት እንደሞቱ ጨምሮ ገልጿል።
የአፍሪቃ ህብረት በትዊተር በገለጸው መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት 187 የህክምና ሰራተኞች ኢቦላ ወደ ተዛመተባቸው የምዕራብ አፍሪቃ ሀገሮች ልኳል።
ዶክተሮችና ነርሶች የሚገኙበት የኢትዮጵያው ቡድን ቀደም ሲል ወደ ሲየራልዮን፣ ላይቤርያና ጊኒ ከተላኩት 175 ናይጀርያውን የህክምና ሰራተኞች ጋር በመሆን በአፍሪቃ ህብረት ተልእኮ ስር እንደሚያገለግል የዐል ጂዚራው ዘገባ ጠቅሷል።
Reliefweb የተባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድረ-ገጽ ደግሞ የዴንማርክ መንግስት ኢሚግረሽን በቅርቡ ኤርትራውያን የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሚመለከት ያወጣው ዘገባ ጥልቅ የሆነ ጉድለት አለበት ይላል።
የዴንማርክና የሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች መንግስታት ኤርትራን በሚመለከት ማንኛውም አይነት የፖሊሲ ለውጥ ከማድረጋቸው በፊት ስለ ኤርትራ ጉዳይ እንዲከታተል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተሰየመው ኮሚሽን የሚያወጣውን ዘገባ መጠበቅ አለባቸው ሲል ሁማን ራትስ ዋች የተባለው የሰብአዊ መብት ድርጅት ያቀረበውን ዘገባ Reliefweb ድረ-ገጽ አውጥቷል። ሙሉውን ቅንብር ያድምጡ።