አለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ታስቦ በዋለበት የዛሬ ቀን የሰደተኞቹን ህይወት ለማትረፍና ሰዎችን ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የሚያሸጋግሩት ሰዎች መድረሻ ያጡትን ሰደተኞች መበዝበዛቸውን እንዲያቆሙ እርምጃ እንዲወሰድ IOM ጥሪ አቅርቧል። በአፍሪቃ ቀንድ ውስጥ ያለውን የስደተኞች ሁኔታን በሚመለከት ኢትዮጵያ የሚገኘው የ IOM ተልእኮ ምክትል ሃላፊ Mr. ጃው ጂያን አብራርተዋል
አለመታዳል ሆኖ ሞት የፍልሰት አካል ሆኖ ቆይቷል። እአአ ከ 2000 አም አንስቶ (ከ 14 አመታት ወዲህ ማለት ነው) በአለም ዙርያ ድንበሮች ተሻግረው ለመሰደድ የሞከሩ ከ 40,000 በላይ የሚሆኑ ፈላሾች አልቀዋል። በተለይም ይህ በመጪው ወር የሚያበቃው አመት የከፋ ነበር። አለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ባወጣው ዘገባ መሰረት በዚህ አመት ብቻ 5,000 የሚሆኑ ሰዎች ባህር ለመሻገር በምደረ-በዳዎችና በተራራዎች ለማለፍ ባደረግዋቸው ጥረቶች ህይወታቸውን አጥተዋል።
ከሙታኑ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ያለቁት በሜድትራንያን ባህር ነው። ከ 3,000 በላይ የሚሆኑ ፈላሾች ሰዎችን ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የሚያሸጋግሩት ሰዎች ባቀረቡላቸው አቅም የሌላቸው ጀልባዎች አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ በሜድትራንያን ባህር ሰምጠዋል።
በየመን በኩል ለማለፍ በሚያደርጉት ጥረት ባህር ውስጥ የሚሰምጡት የአፍሪቃ ቀንድ ስድተኞች ብዛት እንደቀነሰም ተገልጿል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።