በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። የመን ያሉ ህገ-ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች በኢትዮጵያውያንና በሌሎችም የሚፈጽሙት ግፍ የሚል ይገኝባቸዋል።

ብሉምበርግ የተባለው የዜና አገልግሎት የመን ውስጥ ሰዎችን ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የሚያሸጋግሩት ሰዎች በኢትዮጵያውያን ፈላሾች ላይ ግፍና በደል እንደሚፈጽሙ ይገልጻል። ወደ አረብ ባህረ ገብ መሬት በድብቅ ለመግባት ከሀገራቸው የወጡ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በህገወጥ አሻጋጋሪዎች ከሚፈጸሙባቸው በደሎች መካከል ሰቆቃ እንደሚገኝባቸው የዜናው አገልግሎት ጠቅሷል።

ኢትዮጵያውያንና ሌሎች ስደተኞች የመን ሲገቡ ሀገወጥ አሸጋጋሪዎች ጠልፈው ይወስዷቸውና ያላቸውን ገንዘብ ለመዝረፍና ከቤተሰቦቻቸው ከ $1,000.00 ዶላር ባላይ ለማግኘት ሰቆቃ እንደሚፈጽሙባቸው ዘገባው ጠቅሷል። በሰው ህይወት የሚነግዱት ሰዎች የአንዱን ስደተኛ አይን የውሀ ጠርሙስ ሰርጉደው ሲያወጡት እንዳየ መግለጹን ሁማን ራትስ ዋች የተባለው የሰብአዊ መብት ድርጅት እንደጠቀሰ ብሉምበርግ የዜና አገልግሎት ላይ የወጣው ጽሁፍ ጠቁሟል። ሌሎች ርእሶችም አሉን። ያድምጡ።
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG