በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲ የእህትማማችነት ስምምነት ፈርሙ


ከንቲባ ድሪባ ኩማና ከንቲባ ቪንሰንት ግረይ
ከንቲባ ድሪባ ኩማና ከንቲባ ቪንሰንት ግረይ

አዲስ አባባና ዋሽንግተን ዲሲ በእህትማማች ከተማነት ለመተሳሰር ትላንት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ በከንቲባዎቻቸው በኩል ፊርማቸውን አኑረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በዚሁ የፊርማ በአል ለመገኘት ከኢትዮጵያ መጥተው ከዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ Vincent C. Gray ጋር ተቀምጠው ነው ትላንት ማታ ፍርማቸውን ያኖሩት።

የአዲስ አበባና የዋሽንግተን ዲሲ ከተሞች የፊርማ በአል የተጀመረው የኢትዮጵያና የ United States ብሄራዊ መዝሙሮችን በማሰማት ነበር።
ቀጥለው የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ Vincent C. Gray የአዲስ አበባውን ከንቲባ አቶ ዲሪባ ኩማን አስተዋወቁ።

“ከንቲባ ድሪባ ለከንቲባነት ስራቸው ገና አዲስ ናቸው ለማለት ይቻላላ። የፖለቲካ ሙያቸውን የጀመሩት ገና በ 22 አመት እድሜያቸው ነው። ከዚያ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ በድርጅታቸው ውስጥና በአስተዳደር ስራ የተለያዩ እድገቶች አግኝተዋል" ብለዋል።

ከንቲባ ድሪባ ኩማ በበኩላቸው ስለ አዲስ አበባ ብቃት አብራርተዋል።
“እንደሚታወቀው አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊና የኢኮኒሚ ማዕከል ናት። የአፊሪቃ ህብረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪቃ የኢኮኖሚ ኮሚሽንና የሌሎች ክልላዊ ድርጅቶች መቀመጫም ነች። አዲስ አበባ የአከባቢውን የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣትና ለማዳበር የሚችሉ መሪዎችንና የንግድ አፍላቂዎችን ለማገናኘት የሚያስችል ትልቅ ብቃት አላት" ስሉ ከንቲባ ድሪባ አስገንዝበዋል።
AMH-Addis Abeba-Washington-DC-sister-cities-12-12-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:39 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG