በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመጀመርያው ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ


በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ አዲስ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ነው። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቶማስ አኳይናስ አሁን ለጊዜው በካቶሊክ ካቴድራል ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ያለው። በካቶሊክ እምነት የሚመራው ዩኒቨርሲቲ አላማ ሀላፊነት የሚሰማቸው የወደፊት የሀገር መሪዎችን ለማፍራት የታቀደ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው አለም አቀፍ የትምህርት ተቋም እንዲሆን ለማድረግ እንደሆነ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት አቡነ ብርሀነ-የሱስ ገላጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሚሰራው የኢትዮጵያ መንግስት በሰጠው 60 ኤክር መሬት ሲሆን የመጀመርያውን ደረጀ ለመገንባት መሰረተ ልማት የተጣለው ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር ላይ ነው።

አዲስ አበባ የሚመሰረተው ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያው ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚባልውንም ዩኒቨርሲቲ የመሰረተችው ካቶሊካዊት ቤተክስትያን እንደሆነች አስመራ ላይ የነበረው ዩኒቨርሲትም በካቶሊክ ቤተክርስትያን እንደተመሰረተ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ብርሀነ-የሱስ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን አሁን በአዲስ አበባ የምትመሰረተው የመጀመርያው የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ግን በካቶሊክ ቤተክርስትያን የሚመራ እንደሆነ አስገንዝበዋል። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG