ዋሽንግተን ዲሲ —
ህዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲና ለፍትህ የተባለው የኤርትራ ገዢ ፓርቲ እንዲሁም መንግስታዊ ተቋማት ደረጃ በደረጃ ለውጥ የሚደረግባቸው ከወቅቱ ሁኔታ ጋር መራመድ ስላለባቸው ነው ሲሉ ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈውርቂ ተናግረዋል።
ይህ ጉዳይ የሚኒስትሮች ሹም ሽርን ወይም የፖሊሲ ለውጥን የሚያመላክት ነው ወይስ ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ አቶ አላዛር አብረህም የተባሉ ስለኤርትራ ጉዳይ የሚከታትሉ ሰው ሲመልሱ “ሀገሪቱ የምትገኝበትን አጠቃላይ ሁኔታ ስንመለከት የጠባብ መስናክሎችና ማነቆዎች ትግል የሚካሄድባት በመሆኑ ድርጅቱ እአአ በ 1994 አም ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ጉባኤው ቀደም ብሎ መካሄድ ነበረበት። በተለያዩ ማነቆዎችና ጠላታዊ ተግባሮች ምክንያት መሰንክል እየተከሰተ ከጊዚ ወደ ጊዜ ሲሸጋገር ቆይቷል"
ብለዋል።
አቶ አሮን ብርሀነ በበኩላቸው“ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ በነበረው አደረጃጀት ብዙ ወሳኝ የስልጣን ቦታዎች የነበርዋቸው ሰዎች አንድ በአንድ ትተውት ሲሄዱ ቆይተዋል። አንዳንዶቹ ስደት ላይ ነው ያሉት። እነዚህ ሰዎች የፈጠሩት የራሳቸው መረብ ሊኖር ይችላል። ስለሆነም በህዝቡ መካከል ሲጋጋም የቆየውን ተቃውሞና እንቅስቃሴ ለማዳከም የታቀደ ነው" ብለውታል።ዝርዝር ዘገባውን ያድምጡ።