ዋሽንግተን ዲሲ —
ካይሮ ውስጥ ጸረ መንግስት ተቃውሞ ይካሄድባቸው በነበሩት ሰፈሮች ላይ የተወሰደው እርምጃ በመላ ከተማይቱና በመላ ሀገሪቱ ተስፋፍቶ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል።
በግብጽ ወታደራዊ ሃይል የሚደገፈው ጊዚያዊ መንግስት ለደም መፋሰሱ ተጠያቂው የሙስሊም ወድማማችነት ነው ይላል። በካይሮና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ሌሊት የሰአት እላፊ ገደብ ደንግጓል።
ያም ሆኖ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ህንጻዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። በኮፕቲክ አብያተ-ክርስትያንም ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ኮፕቲክ ክርስትያኖች የመሐመድ ሞርሲን ከስልጣን መወገድ ደግፈዋል በሚል ይከስዋቸዋል።
የለዘብተኞች ገጽታ ተደርገው የሚታዩት መሐመድ ኤል-ባራደይ እርምጃውን በመቃወም ከስልጣን የመሰናበት ጥያቄ አቀረቡ።ዝርዝር ዘገባውን ያድምጡ።