በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የሮክ ኤንድ ሮል” ሙዚቃ በአማርኛ፤ የሙዚቃ ወጎች


Jano, the music band
Jano, the music band
 “የሮክ ኤንድ ሮል” ሙዚቃ በአማርኛ፤ የሙዚቃ ወጎች ከኃይሉና ከኪሩቤል ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የሙዚቃ ቡድናቸውም፥ እነርሱም ወጣቶች ናቸው። የጃኖ የሙዚቃ ባንድ አባላት። ድምጻውያኑና ሙዚቀኞቹ በአንድነት በቁጥር አሥር ናቸው።

“ጃኖ” በተባለው የሙዚቃ ቡድናቸው ሥም ባሳተሙት አዲስ ሲዲያቸው አማካኝነት ከሙዚቃ አድማጭ ጆሮ ያደረሷቸውን አሥር ዜማዎች በአጋሮቻቸው ታጅበው በዋና አቀንቃኝነት የተጫወቱት ሁለቱ ድምጻውያን ዲበኩሉ ታፈሰና ኃይሉ አመር ጋ ናቸው፤ በ‘ሮክ እና ሮል’ ስልት ግሩም አድርገው የተጫወቱት።

በዚህ ቅንብር ከድምጻውያኑ ካንዱ ኃይሉ አመርጋ እና ከባንዱ መሪ ክሩቤል ተሥፋዬ ጋር በአዲሱ የሙዚቃ ሲዲያቸው፥ በሙዚቃ ቡድናቸው እና እንዲሁም ሌሎች ሙዚቃ ነክ ርዕሶች ዙሪያ እንወያያለን።

“ራሴን አልዋሽም፥ አልክደውም ምዬ
ሌሎችን አልመስልም እኔነቴን ጥዬ፤

ፈጣሪ ሲፈጥረኝ በእርሱ እኔን መስሎ፥
አንተን መሳይ የለም በዚች ዓለም ብሎ፤

ከውስጥ የማይወጣ የእኔነት ዘር ዘርቷል
እያበበ የሚኖር እውነት አስቀምጧል፤

ለምን ብዬ ራሴን ልዋሽ ደሞ ልርሳ
ሸሽቼ ላላመልጥ ከህሊና ወቀሳ።”

“ራሴን” ይለናል ኃይሉ።

ከኃይሉ አመርጋና ከኪሩቤል ተስፋዬ ጋር የነበረንን የመጀመሪያ ክፍል ወግ ከዚህ ያድምጡ።

 “የሮክ ኤንድ ሮል” ሙዚቃ በአማርኛ፤ የሙዚቃ ወጎች ከኃይሉና ከኪሩቤል ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG