በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ በአዲስ አበባ


ብዙ የአፍሪካ መሪዎች የሰሞኑ የሃገሪቱ የጋሉ ጉዳዮችን በአጀንዳ ይዘው አዲስ አበባ ላይ ለሁለት ቀናት መክረዋል፡፡

የአይቮሪ ኮስትና የሊብያ ጉዳዮች ናቸው የአፍሪካ ሕብረቱ የአዲስ አበባ የከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ምክንያቶች፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ከባድ ውሣኔዎችን እንዲያሣልፉ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ተአማኒነት ጉዳይና የገንዘብም ጉዳይ ሌሎቹ ጠረጴዛ ላይ ያሉ መነጋገሪያዎች ናቸው፡፡

በኅዳሩ ምርጫ አሸናፊነታቸውን ዓለም በስፋት ያረጋገጠላቸውና ዕውቅና የሰጣቸው አላሣን ዋታራ በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል፡፡

በምርጫው መሸነፋቸውን ዓለም በስፋት የተስማማበትና ሥልጣን እንዲለቅቁ አቋም የያዘባቸው ነባሩ ፕሬዚዳንት ሎሮን ባግቦ አልተገኙም፤ ወኪሎቻቸውን ግን ልከዋል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ለአይቮሪ ኮስት ቀውስ መፍትሔ ለመሻት የሰየመው ቡድን ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ረቡዕና ሐሙስን ለሁለት ቀናት ሲመክር ውሏል፡፡

አምስት የአፍሪካ ሃገሮች መሪዎች የሚገኙበት ይህ ቡድን እንዲሁም ወደ አራት መቶ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት የበላው ግጭት ወደተስፋፋ የፖለቲካ ባላንጣነትና አመፃ እንዳያድግ የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ መሆኑ ነው የሚሰማው፡፡

ሎሮን ባግቦ ከዚህ ውይይት ገሸሽ ማለታቸው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች የከበደ ፈተና እንደደቀነባቸው ይሰማል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት ከቡድኑ ስብሰባ በኋላ የሠላምና የፀጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ይጠራል ተብሎ ተጠብቋል፡፡ ሕብረቱ አይቮሪ ኮስትን በተመለከተ የአላሣን ዋታራን አሸናፊነት ያውጃል፤ ሊብያንም ከአባልነት ያግዳል፣ በሃገሪቱም ላይ ከበረራ ነፃ ቀጣና ይከልላል ሲጠበቅ ነበር፡፡

የአፍሪካን ሕብረት በጀት በከፍተኛ ወጭ ከሚደጉሙት አምስት የሰሜን አፍሪካ ሃገሮች አንዷ ሊብያ ወይም መሪዋ መማር ጋዳፊ የመሆናቸው ጉዳይ በራሱ ሕብረቱ ሊያሣልፍ በሚችለው ውሣኔ ፍትሐዊነትና በድርጅቱም ተዓማኒነት ላይ የተደነቀረ ሌላ ፈተና ነው ሲሉ የተለያዩ ታዛቢዎችና ዲፕሎማቶች ተናግዋል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG