በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ሳተላይት ወደ ጠፈር የምታመጥቅበትን ጊዜ አዘገየች


ከሮይተርስ የምስል ክምችት የተወሰደ
ከሮይተርስ የምስል ክምችት የተወሰደ

እኤአ በጥቅምት 2016 ዓመተ-ምህረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ዕውቅና የተቋቋመው የኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ላለፉት ሶስት ዓመታት የኢትዮጵያን ብልጽግና በሚያግዙ ስራዎች ሲወጥን እና ሲሞክር እንደ ሰነበተ ሃላፊዎቹ ይናገራሉ፡፡

የብዙዎችን ትኩረት ከሳበው ሳተላይት ወደ ጠፈር የማምጠቅ ዕቅዱ ወዲያ ፣ ተቋሙ የሳተላይት መቀበያ፣የአቅርቦ ማሳያ ጣቢያዎች ግንባታ እና የመረጃ ማሰባሰብ ስራዎችን ሲያከናውን እንደሰነበተ ተሰምቷል፡፡

ከቻይና መንግስት ጋር በትብብር የሚሰራው የሳተላይት መርሃ ግብሩ በያዝነው መስከረም 2012 ፣በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሚሆነውን መንኮራኩር ወደ ጠፈር ያመጥቃል ተብሎ ዕቅድ ተይዞለት ነበር፡፡ሆኖም ይሄ ዕቅድ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲዘገይ መደረጉን የተቋሙ ሃላፊ ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው የማስወንጨፍ መርሃ-ግብሩ እንዲዘገይ የተደረገበትን ምክንያት እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ማብራሪያዎችን የሰጡበትን ቆይታ ከስር ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ ሳተላይት ወደ ጠፈር የምታመጥቅበትን ጊዜ አዘገየች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:00 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG