በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በእናቴ ስም ልጠራ”:-ቆይታ የእናታቸውን ስም በመጠሪያቸው ከአካተቱ ከያኒያን ጋር


ድምጻዊ እሱባለው ይታየው የሺ፣ ደራሲ እና የባህልና ትውፊት ተመራማሪ አንዱ ዓለም አባተ የአጸደ ልጅ፣ የውዝዋዜ ባለሙያ አብዮት ካሳነሽ
ድምጻዊ እሱባለው ይታየው የሺ፣ ደራሲ እና የባህልና ትውፊት ተመራማሪ አንዱ ዓለም አባተ የአጸደ ልጅ፣ የውዝዋዜ ባለሙያ አብዮት ካሳነሽ

ከተለምዶ ወጣ ባለ መልኩ በመጠሪያ ስማቸው ላይ የእናታቸውን ስም የሚያካትቱ ኢትዮጵያዊያን እየተበራከቱ ነው፡፡ ከዚህ ዑደት ፊታውራሪዎች መካከል የኪነ-ጥበብ ሰዎች ይገኙበታል፡፡

በአባታቸው ስም ተርታ ፣በአያታቸው ስም ምትክ እንዲያም ካልሆነ ደግሞ በመጠሪያቸው መጨረሻ በቅንፍ ውስጥ የእናታቸውን ስም የሚያካትቱ የኪነጥበብ ሰዎች እየበዙ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል ፡-ወጣቱ የሙዚቃ ሰው እሱባለው ይታየው የሺ ፣ደራሲ እና የባህል እና ትውፊት ተመራማሪው አንዱ ዓለም አባተ የአጸደ ልጅ እንዲሁም ዕውቁ ውዝዋዜ ባለሙያው አብዮት ካሳነሽ ይጠቀሳሉ፡፡

የፊታችን እሁድ የሚከበረውን “የእናቶች ቀን” ምክንያት በማድረግ፣ ባልደረባችን ሀብታሙ ስዩም የእናቶቻቸውን ስም ለየት ባለ መልኩ በሙሉ ስማቸው ውስጥ ከአካተቱ ሦስት ታዋቂ የኪነጥበብ ሰዎች ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

“በእናቴ ስም ልጠራ”፤ ቆይታ የእናታቸውን ስም በመጠሪያቸው ከአካተቱ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG