በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያን ድርቅ ለመከላከል ዩናይትድ ስቴይትስ የአስቸኳይ ጊዜ ቡድን ማሰማራት ጀመረች


የዩናይትድ ስቴይትስ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ሰራተኞች ድርቅን ለመከላከል ወደ ኢትዮጵያ ባለሙያዎችን ማሰማራት ጀመረች።

የዩናይትድ ስቴይትስ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ሰራተኞች ድርቅን ለመከላከል ወደ ኢትዮጵያ ባለሙያዎችን ማሰማራት ጀመረች።

እርዳታው ዩናይትድ ስቴይስ አስቀድማ ከሰጠችው 500 ሚሊዮን ዶላርስ ተጨማሪ እንደሆነም ተገልጿል።

ለመጭው የምርት ወቅት ለገበሬዎች ዘር ለማቅርብም ስራ በመስራት እንደሆነ የዩናይትድ ስቴይትስ ተዳድዖ USAID አስተዳዳሪ ጌል ስሚስ አስታውቀዋል።

ለኢትዮጵያ ድርቅ የአሜሪካ ተጨማሪ ድጋፍ፡ 268 + 500 ሚሊዮን ዶላርስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00

በኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጹት፤ የUSAID አስተዳዳሪ ጊል ስሚስ ወደ ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ረዳት ቡድን መላክ ያስፈልገው፤ ሁኔታው ከመባባሱና፤ ሰውነታቸው የተጎዳ ህጻናት ምስል በመገናኛ ብዙሃን መታየት ከመጀመሩ በፊት፤ አስቀድሞ ሁኔታውን ከአጋሮች ጋር ለማረጋጋት ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ በኢትዮጵያ ባደረገው ግምገማ መሰረት ለድርቅ ተጎጂዎች ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት 268 ሚሊዮን ዶላርስ እርዳታ ያስፈልጋል ብሏል።

ዩናይትድ ስቴይስ በኢትዮጵያ የምታሰማራው ቡድን የእርዳታ እንቅስቃሴ፣ የምግብና ውሃ ጥናት ባለሙያዎችና የግልና አካባቢ ንጽህና ጤና ሃኪሞችን ያካትታል።

“በዛሬውለት ይፋ የምናደርገው እርዳታ ለሌሎች ለጋሽ ሀገሮችም ምሳሌ የሚሆን ስልት ነው። ይሄም የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ሰራተኞች ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ማሰማራት ነው። እስካሁን ያለውን አጣዳፊ ስራ የሚያስተባበሩና የሚያሳልጡ ባለሙያዎችን ያካትታል ቡድኑ” ብለዋል የUSAID አስተዳዳሪ ጊል ስሚት።

ቡድኑን የሚመሩት Kate Farnsworth የተባሉና በአስቸኳይ እርዳታ አቅርቦት ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ሴት ናቸው። ከኢትዮጵያ መንግስትና ሌሎች አጋሮች ጋር በትብብር እንደሚሰሩም ተገልጿል።

“ኤል ኒኞ” የሚባለው የአየር ጸባይ ለውጥ ብዙ አካባቢዎችን እያወከ ይገኛል። በደቡባዊ አፍሪካ እየከፋ ሄዷል በላቲን አሜሪካም ጉዳት አድርሷል፤ እንደ ኢትዮጵያ ግን የበረታበት ስፍራ የለም ብለዋል የዩናይትድ ስቴይትስ ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅት USAID ዋና ስራ አስኪያጅ ጊል ስሚት። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ በኢትዮጵያ ባደረገው ግምገማ መሰረት ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት 268 ሚሊዮን ዶላርስ የሚያወጣ እርዳታ ያስፈልጋል።

ዩናይትድ ስቴይትስ በዚህ ረገድ፤ እርዳታ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለው የምርት ወቅት ገበሬዎች ከጉዳታቸውን እንዲያንሰራሩ የሚያስችሉ ስራዎችን አስቀድማ ለማከናወን ያላትን እቅድ ጌል ስሚስ ሲያስረዱ “አራት ሚሊዮን ዶላርስ የሚያወጡ ዘሮችን በፍጥነት እያቀረብን ነው። ገበሬዎች ዝናብ ካገኙና ዘር መዝራት ከቻሉ፤ አሁን ቢቸግራቸውም ለሚቀጥለው የምርት ወቅት ጥገኛ አይሆኑ” ብለዋል።

በኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጹት፤ የUSAID አስተዳዳሪ ጊል ስሚስ ወደ ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ረዳት ቡድን መላክ ያስፈልገው፤ ሁኔታው ከመባባሱና፤ ሰውነታቸው የተጎዳ ህጻናት ምስል በመገናኛ ብዙሃን መታየት ከመጀመሩ በፊት፤ አስቀድሞ ሁኔታውን ከአጋሮች ጋር ለማረጋጋት ነው።

“ድርቁ እስካሁን ጉዳት አላደረሰም ለማለት እንዳልሆነ ይሰመርበት። ከብቶች ሞተዋል። የምግብ እጥረት ጉዳት ምልክቶችም እየጨመሩ ነው። ገበሬዎች ችግር የመቻል ልምዳቸውን ተጠቅመው፤ የሌለ ጥሪታቸውን አሟጠው፤ እጅግ ወደ ከፋ የድህነት አዘቅት ሲገቡ ለማየት አንፈልግም።”

የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታውን የፖለቲካ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንዳይጠቀምበት፤ ከዚህ ቀደም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መረጃ ሲያወጡ እንደነበር ተጠቅሶ የቀረበውን ጥያቄ ሲመልሱ

“እርዳታው በችግሩ ለተጎዱ ሰዎች እንዲደርስ በማንኛውም ስራችን አትኩሮት የምንሰጠው ጉዳይ ነው። በዚህ ረገድ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን በካርታ ላይ አስቀምጠናል። የምግብ እርዳታ የምፈለግባቸው አካባቢዎችን ሰዎች የጉዳት ተጋላጭነታቸው ያየለባቸውን ስፍራዎች ለይተናል። ስለዚህ የምናደርገው ነገር ቢኖር፤ ካርታውን መከተል ነው። የተረጋገጡ ሃቆችና አሃዞችን ይዘን በካርታው እየተመራን በፍጥነት እርዳታ እንዳደርሳለን። ሁለት ሚሊዮን አርብቶ አደሮች በውሃ እጥረት መጎዳታቸውን እናውቃለን። እነዚህ መረጃዎች ናቸው ወደነዚህ አካባቢዎች የሚመሩን።”

ጌል ስሚስ በጋዜጣዊ መግለጫው፤ ሌሎች የአለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች በፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ እርዳታ እንዲያደሱ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ድርቁን ለመከላከል ከፍተኛ በጀት ማቅረቡን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ባለፉት 50 ዓመታት ከታዩ ድርቆች የከፋ ሁኔታ ላይ እንዳለች ተገልጿል።

የኢትዮጵያን ድርቅ ለመከላከል ዩናይትድ ስቴይትስ የአስቸኳይ ጊዜ ቡድን ማሰማራት ጀመረች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG