በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡባዊ አፍሪቃ በ 14 ሚልዮን የሚገመቱ ሰዎች ለረሀብ እንደተጋለጡ የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ


ፍይል ፎቶ - በቫንደርቢል ፓርክ ከጆሃንስበርግ ውጭ የሚገኝ እርሻ እአአ 2015
ፍይል ፎቶ - በቫንደርቢል ፓርክ ከጆሃንስበርግ ውጭ የሚገኝ እርሻ እአአ 2015

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በኤል ኒኖ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ እየከፋ በመሄዱ ቦቆሎ እያለቀባት እንደሆነ ተገልጿል። ደቡብ አፍሪቃ ለአስርት-አመታት ያህል ያልታየ አይነት አስከፊ ድርቅ ተከስቶባታል። ዝናብ በመጥፋቱና ሙቀት እየበረታ በመሄዱ የምግብ ዋጋ እየናረ ነው።

ደቡብ አፍሪቃ ኤል ኒኖ ባስከተለባት ድርቅ ምክንያት ለተከታታይ የምግብ ዋስትና አደጋ ተጋልጣለች። ኤል ኒኖ የተባለው የአየር ለውጥ በየጥቂት አመታት በፓሲፊክ ኢኳቶርያል ክፍል ባለው የውቅያኖስ ጠለል ላይ ውሃው እንዲሞቅ በማድረቅ ድርቅ ያስከትላል።

የደቡብ አፍሪቃ የውሀ ሀይል ዝቅ እያለ ሄዷል። ዋናው የሀገሪቱ ምግብ የሆነው ቦቆሎ ክምችትም እያሽቆለቆለ በመሄዱ ለአራት ወራት ያህል ብቻ የሚያዘልቃት ነው የተረፈው።

“እስከ መጪው ግንቦት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ነጭና ብጫ በቆሎ ሊያጥረን ይችላል። ስለሆነም እስከዛ ባለው ጊዜ ውስጥ በቂ ቦቆሎ እንዲኖረን ማድረግ ይኖርብናል።”

ጠብበብት እንደሚሉት በሰውና በእንስሳት ላይ አስከፊ ረሀብ እንዳይደርስ ለመከላከል ከአንድ ቢልዮን ዶላር በላይ የሚሆን ገንዘብ ያስፈልጋል።

በሰንካል ደቡብ አፍሪቃ እአአ 2016.
በሰንካል ደቡብ አፍሪቃ እአአ 2016.

በደቡባዊ አፍሪቃ በ 14 ሚልዮን የሚገመቱ ሰዎች ረሀብ እንደሚጠብቃቸው የአለም የጤና ድርጅት ዛሬ አስታውቋል። የተቸገሩትን ለመርዳት ከለጋሾች የሚገኘው ገንዘብ እያጠረ በመሄዱ ችግሩ በከባድ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።

ቦትስዋና በአምስት አመታት ውስጥ ያልታየ አይነት ከባድ ድርቅ እንደገጠማት አስታውቃለች። የውሀና የምግብ አቅርቦት እጥረት እየገጠማት እንደሆነም ጨምራ ገልጻለች።

ዚምባብዌም እንደዚሁ በድርቅ ምክንያት አብዛኛው ምርቷ ተኮላሽቶባታል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቁም እንስሳት በድርቅ አልቀዋል። መንግስት በገንዘብ እጦት ምክንያት የመንግስት ሰራተኞችን ደመ-ወዝ በጊዜ ለመክፈል እያቃተው በመሆኑ እነሱም የእንሳቱ እድል እንዳይገጥማቸው ስጋት አለ።

በሚዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ምግብ ማግኘት ሊከድበቸው ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከጆሀንስበርግ የተላከ የቱሶ ኩማሎ (Thuso Khumalo) ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል። አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች ከዚህ በታች ካለው ፋይል ያዳምጡ።

በደቡባዊ አፍሪቃ በ 14 ሚልዮን የሚገመቱ ሰዎች ለረሀብ እንደተጋለጡ የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:40 0:00

XS
SM
MD
LG