በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በራያ ዓዘቦ ዘግይቶ የደረሰው የእህል እርዳታ በቂ አይደለም ተብሏል


በትግራይ ክልል በራያ ዓዘቦ በደረሰው ከፍተኛ ድርቅ የተጠቁ ሰዎች (ፎቶ - ግርማይ ገብሩ)
በትግራይ ክልል በራያ ዓዘቦ በደረሰው ከፍተኛ ድርቅ የተጠቁ ሰዎች (ፎቶ - ግርማይ ገብሩ)

ለ87 ሺህ ሰው ከመስከረም ጀምሮ እርዳታ መድረሱን የወረዳው አስተዳዳር አመልክቷል።

በትግራይ ክልል በራያ ዓዘቦ በደረሰው ከፍተኛ ድርቅ 161 ሺህ ከሚሆነው ከጠቅላላው ሕዝብ 124 ሽው የእህል እርዳታ እንደሚያስፈልገው የወረዳው አስተዳደር ገለፀ።

ለ87 ሺህ ሰው ከመስከረም ጀምሮ እርዳታ መድረሱን የወረዳው አስተዳዳር አመልክቷል።

ከታሕሳስ በኋላ አደጋው እየባሰ በመሄዱ ምክንያት የተረጂው ቁጥር 124 ሺህ መድረሱን አስተዳደሩ የጠቀሰ ሲሆን አስቸኳይ የእህል እርዳታ የሚያስፈልገውና በሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚታቀፈውን ለመለየት በሚል እርዳታው በወቅቱ እንዳልተሰጠ ታውቋል።

ትግራይ ክልል - ራያ ዓዘቦ
ትግራይ ክልል - ራያ ዓዘቦ

በተጨማሪ ደግሞ የእህል እርዳታው ወደ አከባቢው በፍጥነት አለመድረሱንም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ክፍሎም ሃይለ ገልፀዋል።

በነፍስ ወከፍ ለወር የሚሰጠው 15 ኪሎ ስንዴና ግማሽ ሊትር ዘይት በቂ እንዳልሆነ በወረዳው የሐደ አልጋ ገጠር ኗሪዎች የተናገሩትን የወረዳው አስተዳዳሪም ከሰዉ ጋር ተመሣሣይ ሃሣብ እንዳላቸው አመልክተዋል።

የእህል ራሽኑ በአካባቢው ብቻ ሳይሆን በመላ ሃገሪቱ በተሠራጨ መመሪያ መሠረት የተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በሴፍትኔት መርሃግብር በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚኖር ሰው ብዛት ግምት ውስጥ ሳይገባ እህል የሚሰጠው ለአምስቱ ብቻ መሆኑን ለቪኦኤ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎችም አስተዳዳሪውም በአጽንዖት ተናግረዋል።

ወረዳው ውስጥ እስከአሁን በረሃብ ምክንያት የሞተ ሰው የለም ተብሏል።

ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

በራያ ዓዘቦ ዘግይቶ የደረሰው የእህል እርዳታ በቂ አይደለም ተብሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:59 0:00

XS
SM
MD
LG