ሳምንታዊ ዝግጅቶች
በኢትዮጵያ ላይ የተሰናዳው የአሜሪካ ሴኔት ረቂቅ ሕግ ትንታኔ
'በኢትዮጵያ ሰላምና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ለማበረታታት' በሚል ርዕስ በዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤትየውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሴናተር ሮበርት ሜንዴዝ የቀረበውና በሌሎች ሶስት ሴናተሮች ድጋፍ የተደረገለት S-3199 ረቂቅ ህግ ትላንት በኮሚቴው አባላት ከታየ በኃላ ጥቂት ማሻሻያዎች እንደተደረጉበት ተገልጾ አልፏል።
ለመሆኑ ተደረጉ የተባሉት ማሻሽያዎች ምንድን ናቸው፣ በአጠቃላይ የህጉ ይዘቱ ላይስ ለውጥ አምጥቷል ወይ ስንልበደቡብ ካሮላይና የህክምና ዩንቨርስቲ የማህበራዊ ጤና መምህር እና ተመራማሪ እንዲሁም 'ፀጥታና ፍትህ ለትግራይ' የተሰኘው ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ዶክተር ሙሉጌታ ገብረእግዚአብሄር ጠይቀናቸዋል።
ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሚያስቀምጣቸው ማዕቀቦች በኢትዮጵያ ያሉትን ችግሮች ከመፍታት ይልቅሀገሪቱን ወደ በለጠ አለመረጋጋት የሚከት ነው በማለት ተቃውሞውን ሲገልፅ የቆየው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን ህዝብጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ መስፍን ተገኔም፣ የሴኔት ኮሚቴው በረቂህ ህጉ ላይ ተደረገ የተባለው ማሻሽያ፣ማዕቀቦችን የበለጠ የሚያጠናክሩ ናቸው ይላሉ።
S-3199 ረቂቅ ህግ በውጭ ግንኙነት ኮሚቴው ማለፉን ተከትሎ መግለጫ ያወጡት ሴናተር ሜንዴዝ የኮሚቴው አባላትለረቂቅ ህጉ ከፍተና ድጋፍ በማድረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው "ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደላለው የዲፕሎማሲያዊ ጥረት እና ተለዋዋጭ ሁኔታ ወደ ውይይት እና አስተማማኝ ሰላም እንዲገባ አስገዳጅ ጫናየሚያሳድር አቅም በማቅረቡ ኩራት ይሰማኛል" ብለዋል።
ይህ ውሳኔ ግን ረቅቅ ህጉን በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ኢትዮጵያውያኖች ዘንድ የተለያየ ስሜት ፈጥሯል። ህጉተቀባይነት እንዲያገኝ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩት ዶክተር ሙሉጌታ ህጉ በዋናነት በኢትዮጵያ ሰላም እና ዲሞክራሲእንዲሰፍን አስቅውምጧል ያሏቸውን አስገዳጅ ሁኔታዎች እንዲህ ያስረዳሉ።
ረቂቅ ህጉ የአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ በውጪ ሀገር ህግና አቅም ለማስወሰን የተቀመጠ ህን ነው የሚሉት አቶ መስፍንበበኩላቸው ረቂቅ ህጉ ተግባራዊ ቢደረግ በኢትዮጵያ ላይ ሊያደር ይችላል የሚሉትን ጉዳት ይዘረዝራሉ።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ትላንት ያሳለፈው S-3199 ረቂቅ ህግ - ህግ በኢትዮጵያ ላይ ተግባራዊለመደረግ ተጨማሪ ሊያልፍባቸው የሚገቡ ሂደቶች አሉ። እነዚህ ሂደቶች ሁለቱም የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶችእንደሁኔታው አስቸኳይነት እያየ የሚያፈጥናቸው ወይም የሚያዘገያቸው ሲሆን በህግ አውጪው ምክር ቤት ከቀረበውኤች አር 6600 የተሰኘ የውሳኔ ሀሳብ ጋርም የሚዋሃድ እንደሚሆን ዶክተር ሙሉጌታ ያብራራሉ።
በሌላ በኩል አቶ መስፍን ይህ ሂደት ላይሳካ ወይም ረቂቅ ህጉ ፀድቆ ተፈፃሚ ላይግሆን የሚችልባቸው ሂደቶች እንዳሉምያብራራሉ።
አሁን ባለው ሁኔታ የዩናይትድ ስቴትስ የህግ አውጪ እና ህግ አስፈፃሚ ምክርቤቶች በተለያየ ጊዜ ያወጧቸው ኤች አር 66 እና ኤስ 3199 የተሰኙ ረቂቅ ህጎብ በየምክርቤቶች ለመታየት የተመሩባቸውን የውጭ ግንኙነት ኮሚቴዎች ማለፍችለዋል። በቀጣይ በጠቅላላ የምክር ቤቱ ፀድቀውና የፕሬዝዳንቱን ፊርማ አግኝተው ህግ መሆን ይችሉ ወይም አይችሉእንደሆን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።
ተጨማሪ የበጀት ጥያቄና የምጣኔ ሀብት አንድምታው በኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ ለወጣው ወጭና ለደረሰው ጉዳት ማካካሽ የሚሆን የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት በፋይናንስ ሚኒስትር በኩል ጠይቋል፡፡
ቪኦኤ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶ/ር ደግዬ ጎሹ የተጠየቀው ገንዘበ ከሚያስፈልገው በታች መሆኑና መንግሥት የተለያዩ የገቢ ማሰብሰቢያ መርሃ ግብሮችን ማውጣት ያለበት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
ይሁን እንጂ በዚህ ዓመት የቀረበው የበጀት ጥያቄ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ4 እጥፍ በላይ እንደሆነም ተመልክቷል፡፡
ይህ በኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብት ላይ ያለው አዎንታዊና አሉታዊ ጎኑ ምን ይሆናል?
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።