በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰላም፥ ጤና ይስጥልን፥ እንዴት ናችሁ? ራዲዮ መጽሔቶች ነን፥ ከዋሽንግተን ዲሲ፤

አዝናኝና ቁም ነገር አዘል ብቻ ሳይሆኑ፤ ቀደም ሲል ያን ያህል ጎልተው ያልታዩ፥ ትኩረት ጋባዥ ዝግጅቶችና አንዳች ጠያቂ ስሜት በውስጣችን የሚያጭሩ ቅንብሮች ጭምር የሚስተናገዱበት ፕሮግራም ነው -- የራዲዮ መጽሔት።

ሰዓት?

በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች የተካኑ አንጋፋና ወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች በማራኪ ወጎቻቸውን ሊያስደምሙንና በጥበብ ሥራዎቻቸው ሊያዝናኑን ጭምር ቀጠሮ የሚይዙበት የሳምንቱ-መጨረሻ ልዩ ጊዜ፤ እሁድ ምሽት።

ምን?

በተለያዩ ርዕሶች ላይ ያተኮሩ ቃለ ምልልሶች፥ ለዛና ቁምነገር ያዘሉ አዝናኝ ወጎች፥ ሥነ ግጥምና ግሩም ዜማዎች፤ በአጠቃላይም ከጥሩ ራዲዮ ፕሮግራም መስማት የሚሿቸው ቀልብ-ገዢ ዝግጅቶች የሚደመጡበት የእርስዎ ራዲዮ -- የሰንበት ምሽት ምርጫዎ የራዲዮ መጽሔት ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።

የፕሮግራሙ አዘጋጆች፥ አዲሱ አበበና አሉላ ከበደ፤ የአዲስ አበባውን የራዲዮ መጽሔት ልዩ ዘጋቢያችንን ንጉሴ አክሊሉን ይዘን በየአስራ አምስት ቀኑ እሑድ፥ በተለይ ለዕለቱ ከተሰናዱና ከተመረጡ ዝግጅቶቻችን ጋር ብቅ እንላለን። አትጥፉ።

አዎን! እሑድ ከሆነ ዕለቱ፥
የራዲዮ መጽሔት ነው ሰዓቱ አንዱን ዘሎ በሳምንቱ፤

XS
SM
MD
LG