ዜሌንስኪ ድጋፍ ለማሰባሰብ ዋሽንግተንን ጎበኙ

  • ቪኦኤ ዜና

ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ፣ ፕሬዝደንት ባይደን

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አገራቸው ከሩሲያ ጋር ላለባት ጦርነት አሜሪካ ድጋፏን እንድትቀጥል ለማሳመን በትናንትናው ዕለት ኮንግረስን እና ዋይት ሃውስን ጎብኝተዋል።

የአሜሪካ ኮንግረስ ድጋፉን የሚቀጥል ከሆነ፣ ሩሲያ ጦርነቱን በበላይነት እንዳትቀጥል ማድረግ እንደሚያስችላቸው ዜሌንስኪ በጉብኝታችው ወቅት ገልፀዋል።

ዜሌንስኪ በኮንግረስ ባደረጉት ጉብኝት፣ እንደ ከዚህ በፊቱ ለጋራ ም/ቤቱ ንግግር ባያደርጉም፣ ከተወሰኑ አባላት ጋር ሃሳብ ተለዋውጠዋል። የሪፐብሊካን ፓርቲ ዓባላት የሚሰጠውን ድጋፍ በተመለከተ ጥርጣሬ አዘል ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

በዋይት ሃውስ ግን ሞቅ ያለ አቀባበል እንደተደረገላቸው እና ፕሬዝደንት ባይደን ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍ በተመለከተ ኮንግረስ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ‘የሰጥቶ መቀበል’ መፍትሄን እንዳቀረቡ ታውቋል።

ተጨማሪ የ61 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለዩክሬን እንዲሰጥ ባይደን ያቀረቡትን ሃሳብ፣ ሪፐብሊካን የም/ቤት አባላት አዎንታ በመንፈጋቸው ደንቃራ ገጥሞታል።

ዜሌንስኪ በበኩላቸው ዩክሬናውያን ሕይወታቸውን እየሰጡ ያሉት ለአገራቸው ብቻ እንዳልሆነ ተናግረዋል።