ሰሜን ኰሪያ ያደረገችውን የሃይድሮጅን ቦምብ ሙከራ ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች ሌሎች ምዕራባውያን ውድቅ አድርገው ድርጊቱን አውግዘዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ሰሜን ኰሪያ አጥጋቢ የሃይድሮጅን ቦምብ ሙከራ ማድረጓን ዛሬ ረቡዕ አስታወቀች፣ ከዓለም ኃያላን መንግታትም ከፍተኛ ነቀፋን አስከተለባት።
"ሙከራው እራስን ከመከላከል አኳያ የተካሄደ ነው" ሲል መልስ የሰጠው መንግታዊው የሰሜን ኰሪያ መገናኛ አውታር፣ ከዚህ አኳያ "ትንኮሳና ነገር ፍለጋ" ያለውን ዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ ሙከራዎች ጠቅሷል።
ዳሩ ግን ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች ሌሎች ምዕራባውያን፣ የሰሜን ኰሪያውን ማስተባበያ ውድቅ አድርገው ድርጊቱን አውግዘዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለ መሆኑን ያወጣውን መግለጫ ከዚህ በታች ካለው የትዊተር ፋይል ያገኙታል።
በተጨማሪም የዜና ዘገባ አለን የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5