ዘላለም ይትባረክ ለ11 ዓመታት ያህል ሱሰኛ ነበር። በጥቂቱ የጀመራቸው ሱሶች ጓደኞቻቸውን ሰብስበው የተባባሱበት ደግሞ ከአራት ዓመታት በፊት ሲሆን፤ መጠጥ፣ ጫት፣ ሲጋራ፣ እንዲሁም ማሪዋና መጠቀም ጀመረ።
በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት አብረውት ይማሩና ይውሉ የነበሩት የክፍሉ ጓደኞችም በሱስ የተጠመዱ ነበሩ። ዘላለም ሲያስረዳ፤ አልፎ አልፎ ለመዝናናት ሳይሆን፤ ቀናቸውና ውሏቸው፣ ገንዘባቸው፤ ሃሳባቸው፣ የወጣት ሃይላቸው በሙሉ በሱስ ላይ ያተኮረ ነበር።
“ትናንት በነበረኝ ህይወት የምኖረው ለሲጋራ ነው፤ ለአንድ ብር ሲጋራ” ይላል መለስ ብሎ ያሳለፈውን ሁኔታ ሲያስረዳል። ዘላለምና ጓደኞቹ ተሰባስበው አንድ ሃሳብ አፈለቁ። በቅድሚያ እራሳችንን ከሱስ እናላቅ፤ እንረዳዳ፤ እንተባበር ሲሉ።
ተሳክቶላቸው ከሱስ ነጻ ሆኑ። ከሱስ ነጻ የመሆነ ፈተናው ማቆም ብቻ እንዳልሆነም ተረዱ። አጠቃላይ የሆነ የህይወት ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነም በመተማመን፤ ህይወታቸውን ለወጡ። ቀጣዩ ጉዟቸው የሌሎች ወጣት ሱሰኞችን ህይወት መገዝ እንደሆነ በማሰብ “መቋሚያ” የተሰኘች የማህበረሰብ ድርጅት መሰረቱ።
“መቋሚያ” ከአደንዛዥ እጽና አደንዛዥ አስተሳሰብ የተነሳ ሰዎች ሊደክማቸው መደገፍ እንዲችሉበት መማሰብ ነው ይላል ዘላለም ይትባረክ። የአደንዛዥ አስተሳሰብ መገለጫዎች “አልችልም፣ አይሆንልኝም፣ ሙሰኝነት፣ ኃላፊነትን አለመወጣት፣ ለሌሎች አለማሰብ፣ ስግብግብነት፣ አገርን አለመውደድ” ናቸው።
ልዩነቱ ይላል ዘላለም፤ አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚውን ሲያጠቃ፤ አደንዛዥ አስተሳሰብ ግን ማህበረሰብን በአጠቃላይ ያውካሉ። ዝርዝሩን ከቃለመጠይቁ ያግኙ።
Your browser doesn’t support HTML5