ኃይሌ ገብረሥላሴ ውድድር አቆመ

  • ሰሎሞን ክፍሌ
በዛሬው ሳምንታዊ የስፖርት ፕሮግራማችን ኃይሌ ገብረ ሥላሴ መሰናበቱን፣ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሻምፒዮን እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር መጀመሩን እና ሌሎች ዜናዎችን ይዘናል።

የዓለማችን ታላቁ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በ 15ኛው የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ላይ በይፋ ከአትሌቲክሱ ዓለም ተሰናበተ።

12 ሀገሮች የሚሳተፉበት የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሻምፒዮን እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በኢትዮጵያ ተጀመረ። አስተናጋጅ ኢትዮጵያ በሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን 1 ለ 0 ተሸነፈች። በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የተጀመረው የሴካፋ ውድድር እስከ ህዳር 26 ቀን 2008 ዓም ይቆያል።

በስፔን ላ ሊጋ (La Liga) ባርሴሎና በእንግሊዙ ፕሪምየር ሊግ ደግሞ ሌስተር ሲቲ የደረጃ ሠንጠረዡን እየመሩ ናቸው።

Your browser doesn’t support HTML5

ኃይሌ ገብረሥላሴ ውድድር አቆመ

የኃይሌ ገብረ ሥላሴን የረጅም ርቀት ኃያልነትና የሩጫ ዘመኑ ትውስታዎች፣ ከዚህ በታች ያሉትን የፎቶ መድብሎችን ይመልከቱ።

ኃያሉ ኃይሌ፡- ታሪካዊ ፎቶዎች